Germa Mogeseh Lyrics
ዛሬማ ዓይኔ ያየው በለጠ ጆሮዬ ከሰማው በላዬ ስለ ሾምኩህ ልቤን ኩራት አለው (፪x) ንግሥናህን ሳስበው ውስጤ ተደንቀ መገረም ተሞላ አንድ ነህ ለሕይወቴ አላውቅም ከአንተ ሌላ የለኝም ከአንተ ሌላ
እንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው ንጉሥ ወግህ ስርዓትህ ሆ ኧረ እንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው አገዛዝህ ቅን ነው ፍርድህ (፪x)
ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም (፬x)
ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም ልዩ ነህ አንተ አልጠገብኩህም (፪x)
ማለዳም ማለዳ አዲስነትህ ነው ልዩ ያደረገህ ዕድሜውን ከአንተ ጋራ ፈጅቶ የትኛው ሰው ለመደህ የትኛው ሰው ጠገበህ ከትላንትናው ዛሬ ከዛሬው ነገ ይለያል የክብርህ ነፀብራቁ ስለዚህ በልጠህብኛል ከአልማዝ ከወርቅ ከዕንቁ (፪x)
ጆሮዬ ድምጽን ሰምቶ አይጠግብም ዓይኔ ክብርህን አይቶ አይጠግብም ምላሴ ጽድቅህን አውርቶ አይጠግብም ቃላቴ አደናንቆህ አይጠግብም
ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም (፬x)
ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም ልዩ ነህ አንተ አልጠገብኩህም (፪x)
እንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው ንጉሥ ወግህ ስርዓትህ ሆ ኧረ አንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው አገዛዝህ ቅን ነው ፍርድህ (፪x)
ተወዳዳሪ አቻ እና እኩያ የለህም ልዩ ነህ ለዘላለም (፬x)
ከጉባዔው መሃል ብዙ ሕዝብም ካለበት ተጋባዥ ሰው ሆኜ ያኔ በፍርሃት ህዝቡ ብዙ ግን ባንድ ድምፅ አቤት ዝማርያቸው መፅሐፍ ተከፍቶ ይነገራል ሰምቼ ማላውቀው (፪x)
ከቃሉ የህይወት ውሃ ወደልቤ ፈሰሰ ሳላቅማማ ጠጣሁት ውስጤም ረሰረስ ኧረ እንዴት ያለ ቀን ነው ዳግመኛ ተወለድኩኝ በልቤ አምኝ በአፌም መሰከርኩኝ
በዚያን ቀን አሃሃ ታሪኬ ተቀየረ በዚያን ቀን ኦሆሆ ቀንበሬ ተሰበረ በዚያን ቀን ሽክሜም ቀለለልኝ በዚያን ቀን ኢየሱስ ጌታ ነው አልኩኝ
እንዳንተ ያለ ጌታ አንተን መሳይ ወዳጅ እንዳንተ ያለ መሃሪ አንተን መሳይ አምላክ
ለማወቅ ተከፈቱ ዓይኖቼ የመዳንን ቃል ሰምቼ ወስኜ አንተን ያገኘሁባት ያችን ቀን አልረሳት ያችን ቀን ልባርካት (፪x)
ውዴ ደጁን ሲያንኳኳ በሬን ከፈትኩለት ከእኔ ጋር እራት በላ የዋህ ነው በልቡ ትሁት ተቆረሰ የሕይወት እንጀራ ዓይኖቼም ተከፈቱ እንደንቦሳ ዘለልኩኝ አይረሳኝም ዕለቱ
በዚያን ቀን አሃሃ ኃጢያቴ ተሰረየ በዚያን ቀን ኦሆሆ በሰማይ ደስታ ሆነ በዚያን ቀን በአብ ቀኝ ተቀመጥኩኝ በዚያን ቀን አምላክን እኔ ወረስኩኝ
እንዳንተ ያለ ጌታ አንተን መሳይ ወዳጅ እንዳንተ ያለ መሃሪ አንተን መሳይ አምላክ
ለማወቅ ተከፈቱ ዓይኖቼ የመዳንን ቃል ሰምቼ ወስኜ አንተን ያገኘሁባት ያችን ቀን አልረሳት ያችን ቀን ልባርካት (፪x)
ይገርማል እኔን መውደድህ ይገርማል ይገርማል እኔን ማሰብህ ይገርማል (፪x)
ይገርማል እኔን መውደድህ ይገርማል እኔን ማሰብህ ይገርማል እኔን ማፍቀርህ ይገርማል (፫x)
ሥምህን ስጠራ በከንፈሮቼ ደጋግመው ይለኛል መላው እኔነቴ እስቲ ልደጋግመው ኢየሱሴ ብዬ በረከቴ እኮ ነው ለነፍሴ ተድላዬ
ስደጋግመውማ (፪x) ኑሮዬ ይባረካል ሰላሜ ይበዛልኛል ኑሮዬ ይባረካል ደስታዬ ይበዛልኛል
እወድሃለሁ ስልህ ከልቤ እንደሆነ አንተው ታውቀዋለህ (፪x) እራስህ ታውቀዋለህ (፪x) እከተላለው ስልህ ወስኜ እንደሆነ ልቤን ታውቀዋለህ (፪x) ውስጤንም ታውቀዋለህ (፪x)
የማይጠገብ ጣዕም የማያልቅ መዓዛዉ ፍጥረት ተደነቀ ጌታዬን ስጠራዉ እኔም አላረፍኩ አበዛሁ መጥራትን ኢየሱስ ጌታ ነው ኦሆ አዳኝ ነው ማለት
ስደጋግመውማ (፪x) ደረቁ ይለመልማል አበባው ፍሬን ይሰጣል ደረቁ ይለመልማል ቡቃያው ይሰጣል
እወድሃለሁ ስልህ ከልቤ እንደሆነ አንተው ታውቀዋለህ (፪x) እራስህ ታውቀዋለህ (፪x)
እከተላለው ስልህ ወስኜ እንደሆነ ልቤን ታውቀዋለህ (፪x) ውስጤንም ታውቀዋለህ (፪x)
በጠዋት በማታ ስሙን ሳነሳሳው ለእኔ ድል ሆነኝ ለጠላት አበሳ ኢየሱስ ስልበት ጠላት ተሸበረ መንግስቱ ፈረሰ ወጥመድ ተሰበረ
ስደጋግመውማ (፪x) ጠላቴ ይዋረዳል ሽንፈቱን ይከናንባል ጠላቴ ይዋረዳል ምርኮዬን ይመልሰዋል
እወድሃለሁ ስልህ ከልቤ እንደሆነ አንተው ታውቀዋለህ (፪x) እራስህ ታውቀዋለህ (፪x) እከተላለው ስልህ ወስኜ እንደሆነ ልቤን ታውቀዋለህ (፪x) ውስጤንም ታውቀዋለህ (፪x)
ልቤ አንተን ይላል መንፈሴም ወዳንተ ይገሰግሳል ጉጉቴ አንተን ማክበር ነው ፍላጎቴ ክብርህን ማየት ነው
የእኔ ደስታ አንተን ማስደሰት ነው ዓላማዬ የአንተ ዓላማ ነው የእኔ ደስታ ደስ ሲልህ ማየት ነው ዓላማዬ የአንተ ዓላማ ነው
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (፪x)
ከምትወደው ጋራ እስማምለሁ የምትጠላው ለኔ ጠላቴ ነው በመታዘዝ ፍቅሬን እገልጻለሁ ዝቅ ማለቴ አንተን ከፍ ላደርግ ነው
መኖር ትርጉም ሚስጥሩ አንተ ነህ እወዳለሁ ዛሬም ልገዛልህ (፪x)
ዋላ ወደውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ነፍሴ አንተን ተጠማች ነፍሴ አንተን ተጠማች (፪x)
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (፪x)
እንደልብህ ሆኜ ልኑርልህ ልቤን ትቼ ያየኸውን ልይልህ መንፈስን ከኔ አትውሰደው አጥፍ ልስገድ ሁሌም ላገልግለው
ከውሃ ውስጥ እንደወጣ ዓሣ መኖር አልችልም ተለይቼ ጌታ (፪x)
ዋላ ወደውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ነፍሴ አንተን ተጠማች ነፍሴ አንተን ተጠማች (፪x)
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (፪x)
እንዲህ የምሆነው በዚህ ጉብዝናዬ
ያረፈበት ዓይኔ የወደደው ልቤ በኢየሱስ ቁንጅና ላይ ነው ያለው ሀሳቤ ያረፈበት ዓይኔ የወደደው ቀልቤ በኢየሱስ ቁንጅና ላይ ነው ያለው ሃሳቤ
ፍጥረት በሙሉ ይየው ይየው ጌታን ይየው አንዴ ቀምሶ ካጣጣመው ሌላ አያሰኘው
ሌላውን ላልወድ ሌላዉን ላልሻ በሌላ ላልታለል ሌላዉን ላልሻ ተማርኬያለሁ እስከመጨረሻ (፪x) አመልከዋለሁ እስከመጨረሻ (፪x)
ያገር ቆንጆ ነኝ ባዩ ከውዴ ሲተያዩ ያመረ መሳይ ዉበቱ ዉዴ ይበልጠዋል በስንቱ ያገር ቆንጆ ነኝ ባዩ ከየሱስ ሲተያዩ ያመረ መሳይ ዉበት ዉዴ በዛበት በስንቱ
ፍጥረት በሙሉ ይየዉ ይየው ጌታን ይየዉ አንዴ ቀምሶ ካጣጣመዉ ሌላ አያሰኘዉ
እንዲህ የምሆነው (፪x) የኢየሱስ ውበቱ ከሁሉ በልጦብኝ ነው በዚህ ጉብዝናዬ ለዓለም ማልገዛው ያዘጋጀው ክብር ከዓለም በልጦብኝ ነው (፪x)
አገር ሁሉ ያደነቀው ሰዓሊው የሳለው አይ ሞኙ መች ገባው የኔን ቆንጆን አላየው አገር ሁሉ ያደነቀው ሰዓሊው የሳለው አይ ሞኙ መች ገባው ኢየሱሴን አላየው
ፍጥረት በሙሉ ይየዉ ይየው ጌታን ይየዉ አንዴ ቀምሶ ካጣጣመዉ ሌላ አያሰኘዉ
ውበትን ላላፈልግ ዓለምን ላልሻ በዓለም ላላታለል ውበትን ላልሻ አግኘቸዋለሁ እስከመጨረሻ (፪x) ወርሼዋለሁ እስከመጨረሻ (፪x)
እንዲህ የምሆነው (፪x) የኢየሱስ ውበቱ ከሁሉ በልጦብኝ ነው በዚህ ጉብዝናዬ ለዓለም ማልገዛው ያዘጋጀው ክብር ከዓለም በልጦብኝ ነው (፬x)
በጥበብህ በችሎታህ እንዳንተ ያለ ማነው ጌታ (፪x) ዕውቀትህ የተለየ ፍጥረት እንዳንተ አልሰማ አላየ (፪x)
(አሃሃ) ትልቅ ነህ ብልህም (አሃሃ) ከዚያም ትልቃለህ (አሃሃ) ጌታዬ እግዚአብሔር (አሃሃ) በማን ልመስልህ
ከምልህ በላይ ነህ የኔ ጌታ (፬x)
ሰው ከፍታ መጨረሻ መርገጫህ ነው ላንተ መነሻ (፪x) ታች ብወርድ ላይ ቢወጣ የሚመስልህ አንድም ታጣ ታች ብወርድ ላይ ቢወጣ የሚያህልህ አንድም ታጣ
(አሃሃ) ከህዝብህ ጋር ሆኜ (አሃሃ) ስምህን ባውድስ (አሃሃ) እንኳን ልጨርሰው (አሃሃ) ከመሃሉም እልደርስ
ጥበብህ ብዙ ነው የኔ ጌታ (፪x) ዕውቀትህ ሠፊ ነው የኔ ጌታ (፪x)
ገዢዎችን ትሾማለህ ሲያሻህ ደግሞ ታወርዳለህ ገዢዎችን ትሾማለህ ሲያሻህ ደግሞ ትሽራለህ ልዕልናህ እጅግ ከፍ ያለ ካንተ በላይ ማንም የለ (፪x)
(አሃሃ) ከህዝብህ ጋር ሆኜ (አሃሃ) ስምህን ባውድስ (አሃሃ) እንኳን ልጨርሰው (አሃሃ) ከመሃሉም እልደርስ
ከምልህ በላይ ነህ የኔ ጌታ (፪x) ልገልፅህ አልችልም የኔ ጌታ (፪x)
ላምልክ እንደገና አሃ (፫x) አምላኬ ነህና ላንግሥ እንደገና አሃ (፫x) ንጉሤ ነህና (፪x)
አዝ፦ እወድሃለሁ ወዳጄ (፪x)
እወድሃለሁ ኦሆሆ ፍቅርህን እያየሁ
አፈቅርሃለሁ ወዳጄ (፪x)
አፈቅርሃለሁ ኦሆሆ ፍቅርህን እያየሁ
መች ቀረሁ ስላንተ ሰምቼ
አወኩህ አንተ ተጠግቼ (፪x)
አልናከኝም ተቀብለኸኛል
ልጅህም ምክንያት ሆኖልኛል
ኢየሱስ ምክንያት ሆኖልኛል
ምክንያቱ አንተ ነህ ሥምህን ለመጥራቴ አዎ (፪x)
ምክንያቱ አንተ ነህ ቤትህ ለመኖሬ አዎ (፪x)
በትንሿ ልቤ ስትገባ
መውደዴን ገለፅኩልህ በእንባ
ምን ልበል ኧረ እኔስ ምን ልናገር
ከማምለክ ከማመስገን በቀር
ምን ልበል ኧረ እኔስ ምን ልናገር
በትንሿ ልቤ ስትገባ
ማፍቀሬን ገለፅኩልህ በእንባ
ምን ልበል ኧረ እኔስ ምን ልናገር
ለቃልህ ከመሸነፍ በቀር
ምን ልበል ኧረ እኔስ ምን ልናገር
አዝ፦ እወድሃለሁ ወዳጄ (፪x)
እወድሃለሁ ኦሆሆ ፍቅርህን እያየሁ
አፈቅርሃለሁ ወዳጄ (፪x)
አፈቅርሃለሁ ኦሆሆ ፍቅርህን እያየሁ
ለፍቅሬ መግለጫ ቋንቋ ቢያጥረኝ እንኳን
ግን ላወራ ልናገረው ዝም ከማለት ቢሻል
የገረመኝ መዳኔ ነው እያልኩኝ ሳውራ
ድንቅህን አሳየኸኝ በዘመኔ በየተራ
ትገርማለህ ታስገርማለህ
ትገርማለህ አንተ
ትገርማለህ ታስገርማለህ
ትደንቃለህ አንተ
አዝ፦ እወድሃለሁ ወዳጄ (፪x)
እወድሃለሁ ኦሆሆ ፍቅርህን እያየሁ
አፈቅርሃለሁ ወዳጄ (፪x)
አፈቅርሃለሁ ኦሆሆ ፍቅርህን እያየሁ
አልቀረሁ ስላንተ ሰምቼ
አወኩህ አንተ ተጠግቼ (፪x)
አልናከኝም ተቀብለኸኛል
ልጅህም ምክንያት ሆኖልኛል
ኢየሱስ ምክንያት ሆኖልኛል
ምክንያቱ አንተ ነህ ልጅህ ለመሆኔ አዎ (፪x)
ምክንያቱ አንተ ነህ አባት ለማግኘቴ አዎ (፪x)
ሰማያት ያንጠባጠቡት ዝናብ ቀላያትም የያዙት ውኃ
የምድርን ዛፎች ባስተባብር በደን ያሉ በበረሃ
አሃሃ ውኃው ቀለም ቢሆን አሃሃ ዛፉም ደግሞ ብዕር
አሃሃ ሁለቱም ቢጣመሩ አሃሃ ክብርህን እንዲያወሩ
አዝ፦ ብዕሬ እንኳን አንደበት ኖሮት ቢፈጠር
ኧረ ስንቱን ስንቱን ይናገር ነበር (፪x)
ተራ ንጉስ ቤት እንኳን ገብቼ
ስለእርሱና ዘሩ ቀለሜን በከንቱ ጨርሼ
ንጉሥ ዘውዱን ሲደፋ የጻፍኩት አኔው ሰምቼ
ሲሻር ሲዋረድ ተረኩት ደግሞ መልሼ
አሃሃ ሰልችቶኛል ስተርከው የምድሩን
አሃሃ ግራ ይገባኝ ሲሾሙና ሲሻሩ
አሃሃ ምን አለ ሰዎች የላዩን ብትጽፉብኝ
አሃሃ የምድሩን ከማውራት መተረክ ብትገላግሉኝ
አሃሃ ጥሜ እንዲረካ የልቤ እንዲደርስ
አሃሃ እጅግ ደስ ይለኛል ቀለሜን ስለእርሱ ብጨርስ
አዝ፦ ብዕሬ እንኳን አንደበት ኖሮት ቢፈጠር
ኧረ ስንቱን ስንቱን ይናገር ነበር (፪x)
ወዶ አፍቅሮ ሲያስብ ሰው በልቡ
ይጠበብብኛል ለመግለፅ የውስጥ ሃሳቡ
ወደድኩኝ ባለበት ቅፅበት ጠላሁ ደግሞ ይልብኛል
ወረት ያለው ፍቅር ለእኔስ ግራ ገብቶኛል
አሃሃ ሰልችቶኛል ስተርከው የምድሩን
አሃሃ ግራ ይገባኛል ስዋደዱ ሲጣሉ
አሃሃ ምን አለ ሰዎች የላዩን ብትጽፉብኝ
አሃሃ የምድሩን ከማውራት መተረክ ብትገላግሉኘ
አሃሃ ጥሜ እንዲረካ የልቤ እንዲደርስ
አሃሃ እጅግ ደስ ይለኛል ቀለሜን ስለእርሱ ብጨርስ
አዝ፦ ብዕሬ እንኳን አንደበት ኖሮት ቢፈጠር
ኧረ ስንቱን ስንቱን ይናገር ነበር (፪x)
ከድሮ ጀምሮ ሁኔታው የማይቀየር
እንዳለ የነበረ እንዲሁ ደግሞ የሚኖር
ጥንት ስለእርሱ የጻፍኩት ያው ነው አልቀየርኩት
ከትውልድ ትውልድ ይሄው አሳለፍኩት
አሃሃ ስለመለወጡ ሁሌ የማልሰጋበት
አሃሃ ከሁሉ የተለየ ጽናትን ያየሁበት
አሃሃ ብጀምር ላወራ ስለእርሱ መስሎኝ አንደሰው
አሃሃ ቀለሜ አለቀ እንጂ እሱንማ መች ልጨርሰው
አሃሃ ብቀጥል ላወራ ስለእርሱ መስሎኝ እንደሰው
አሃሃ አኔ አለኩ እንጂ ዘመኑን መች ልጨርሰው
አዝ፦ ብዕሬ እንኳን አንደበት ኖሮት ቢፈጠር
ኧረ ስንቱን ስንቱን ይናገር ነበር (፪x)
አዝ፦ ምስክር ነኝ እኔ አምላክ እንደሆንክ
ምስክር ነኝ እኔ ጌታ እንደሆንክ
እመሰክራለሁ እንደምትረዳ
ምስክር ነኝ እኔ እንደምትደርስ ለተጐዳ
እኔን ያዩ ዓይኖችህ ይባረኩ ለዘላለም
እኔን የሰሙ ጆሮዋችህ ይባረኩ ለዘላለም
እኔን ያነሱ እጆችህ ይባረኩ ለዘላለም
እኔን ያጽናኑ ቃሎችህ ይባረኩ ለዘላለም
በሰማይ ተቀምጠህ ከፍ ባለ ስፍራ
በምድር ሆኜ ትንሽ ሰው እርዳኝ ብዬ ስጣራ
ሰምተህ ከመለስከኝ ቀኝህ ከረዳችኝ
ላመስግን በዘመኔ ክንድህ ካገዘችኝ
ኦሆ ክንድህ ካገዘችኝ
አዝ፦ ምስክር ነኝ እኔ አምላክ እንደሆንክ
ምስክር ነኝ እኔ ጌታ እንደሆንክ
እመሰክራለሁ እንደምትረዳ
ምስክር ነኝ እኔ እንደምትደርስ ለተጐዳ
እኔን ያዩ ዓይኖችህ ይባረኩ ለዘላለም
እኔን የሰሙ ጆሮዋችህ ይባረኩ ለዘላለም
እኔን ያነሱ እጆችህ ይባረኩ ለዘላለም
እኔን ያጽናኑ ቃሎችህ ይባረኩ ለዘላለም
ዮርዳኖስ ሲከፈል ተዓምር ማሳያ
ከመሃል ድንጋይ ወጣ ሆነ መታሰቢያ
እኔም በዚህ ዘመን ሥራህን ስላየሁ
ሕያው ለመሆንህ ምስክር እሆናለሁ
ኦሆ ምስክር እሆናለሁ
እንኳን ወዳጆቼ እዚህ መድረሴ እኔም ለእራሴ
አስቤው አላውቅም በህልሜም በውኔ (፪x)
ጠላቶቼማ የኔን ውድቀት የሚሹ
አሳፈርካቸዉ ታምራትህን አዩ (፪x)
በለቅሶ ተዘርቶ በደስታ ከታጨደ
በኩርንችት ፈንታ ባርሰነት ከበቀለ
ንጉሥ ለሚወደው ሰው እንዲህ ይደረጋል
ማይጠፋ ምልክት ነው ዓይኔ ይህን አይቷል
ኦሆ ዓይኔ ይህን አይቷል
አዝ፦ ምስክር ነኝ እኔ አምላክ እንደሆንክ
ምስክር ነኝ እኔ ጌታ እንደሆንክ
እመሰክራለሁ እንደምትረዳ
ምስክር ነኝ እኔ እንደምትደርስ ለተጐዳ
እኔን ያዩ ዓይኖችህ ይባረኩ ለዘላለም
እኔን የሰሙ ጆሮዋችህ ይባረኩ ለዘላለም
እኔን ያነሱ እጆችህ ይባረኩ ለዘላለም
እኔን ያጽናኑ ቃሎችህ ይባረኩ ለዘላለም
እንኳን ወዳጆቼ እዚህ መድረሴ እኔም ለእራሴ
አስቤው አላውቅም በህልሜም በውኔ (፪x)
ጠላቶቼማ የኔን ውድቀት የሚሹ
አሳፈርካቸዉ ታምራትህን አዩ (፪x)
በሰማይ በምድር የከበርከው
ከጥንትም ጀምሮ የነበርከው (፪x)
ዙፋንህ ከፍ ያለ የፀና
እግዚአብሔር ብቻህን ገናና (፫x)
ገናና ብቻህን ገናና
ገናና ብቻህን ነህ ገናና
ለሁሉም ምዕራፍ መጀመሪያቸው
መውጣትና መግባት ሁሉ በእጅህ ነው
ባለዝና ነህ ሁሉም ያውቅሃል
ገናናነትህ ደግሞ ዓለምን ሞልቷል
የከበረ የነገስህ ከፍ ያልህ የበረታህ
እግዚአብሔር ብቻ ጌታ ነህ (፪x)
አምላኬ ብቻ ጌታ ነህ (፪x)
በሰማይ በምድር የከበርከው
ከጥንትም ጀምሮ የነበርከው (፪x)
ዙፋንህ ከፍ ያለ የፀና
እግዚአብሔር ብቻህን ገናና (፫)
ገናና ብቻህን ገናና
ገናና ብቻህን ነህ ገናና
አማልክት ተብለው እጅግ ተፈርተው
የሰዎች ሥራዋች ፍጡር ፈጥሩዋችው
አይሰሙ አያዩ ደግሞ አይመልሱ
ላወዳድርህ ነው ወይ አንተን ከእነሱ
ከእንግዲህ በእኔ ዘር ከኔ በኋላ
አይመለክም ካንተ ሌላ
አይመለክም ካንተ ሌላ (፪x)
ወደር የሌለህ አቻ የሌለህ
መሳይ የሌለህ አቻ የሌለህ (፪x)
ሰማይ ተቀምጠህ ምድር የምትረግጥ
ትላንት ዛሬ ነገ የማትለወጥ
እረጅምና ከፍ ያለ ዙፋንህ
የማይቆጠር ነው እድሜ ዘመንህ
ከእንግዲህ በእኔ ዘር ከኔ በኋላ
አይሰበክም ካንተ ሌላ (፪x)
ከእንግዲህ በእኔ ዘር ከኔ በኋላ
አይለመንም ካንተ ሌላ (፪x)
ሌላ አይለመንም ካንተ ሌላ
ሌላ ሌላ አይለመንም ካንተ ሌላ
ሌላ ከብሮ አይታይም ካንተ ሌላ
ሌላ ሌላ ነግሶ አይታይም ካንተ ሌላ
ወደር የሌለህ አቻ የሌለህ
መሳይ የሌለህ አቻ የሌለህ (፪x)
ግልሙትናዋ እጅግ ስለበዛ
ሥራዋ አይቆምም ጻዲቅ ካልተነሳ
የነብያትና የቅዱሳን ጠላት
ጻድቅ ታጥቀህ ውጣ እርሱዋን ተበቀላት
ኤልዛቤል ትዋረዳለች
ኤልዛቤል ውሾች ይበሏታል
ኤልዛቤል ትዋረዳለች
ኤልዛቤል ሥራዋ ይፈርሳል [1]
ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (፬x)
በዚህ ዘመን ሕዝቡን ያራደ ያንቀጠቀጠ
እሱ ማን ነው (፫x)
የእግዚአብሔር የእቃ ጦር ለብሶ
ጻድቅ ይጋጠመው (፫x)
ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (፬x)
ጉልበት ሆኖለታል እግዚአብሔር አምላኩ
በእምነት እሮጠ እየያ ፊት ፊቱ
አልተመለሰም ከቶ ወደ ኋላ
ተስፋው አምላኩ ነው አያይም ሌላ (፪x)
በልዑል አምላክ ሥም ተማምኖ
በትከሻው መሃል አድሮ
ቅድስና ለእግዚአብሔር ብሎ
ይኖራል ጌታውን አክብሮ
ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (፬x)
የእግዚአብሔር ዓይኖች ያረፉበትን ሰው
ባዶ የምታደርግ የምታስቀር ላጭታው
አልያዝም የሚል ደግሞ የጨከነ
እርሷን የሚያዋርድ ጻድቅ ወዴት አለ
ደሊላ ትዋረዳለች
ደሊላ ጌታ ይበቀላታል
ደሊላ ትዋረዳለች
ደሊላ ሥራዋ ይፈርሳል
ደሙ በግንባሩ ሆኖ በመቃኑ
እንዳይነካ እምላክ ከእርሱ ጋራ ነው ለካ (፪x)
ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (፬x)
ግልሙትናዋ እጅግ ስለበዛ
ሥራዋ አይቆምም ጻዲቅ ካልተነሳ
የነብያትና የቅዱሳን ጠላት
ጻድቅ ታጥቀህ ውጣ እርሱዋን ተበቀላት
ኤልዛቤል ትዋረዳለች
ኤልዛቤል ውሾች ይበሏታል
ኤልዛቤል ትዋረዳለች
ኤልዛቤል ሥራዋ ይፈርሳል [1]
ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (፬x)
በዚህ ዘመን ሕዝቡን ያራደ ያንቀጠቀጠ
እሱ ማን ነው (፫x)
የእግዚአብሔር የእቃ ጦር ለብሶ
ጻድቅ ይጋጠመው (፫x)
ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (፬x)
ጉልበት ሆኖለታል እግዚአብሔር አምላኩ
በእምነት እሮጠ እየያ ፊት ፊቱ
አልተመለሰም ከቶ ወደ ኋላ
ተስፋው አምላኩ ነው አያይም ሌላ (፪x)
በልዑል አምላክ ሥም ተማምኖ
በትከሻው መሃል አድሮ
ቅድስና ለእግዚአብሔር ብሎ
ይኖራል ጌታውን አክብሮ
ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (፬x)
የእግዚአብሔር ዓይኖች ያረፉበትን ሰው
ባዶ የምታደርግ የምታስቀር ላጭታው
አልያዝም የሚል ደግሞ የጨከነ
እርሷን የሚያዋርድ ጻድቅ ወዴት አለ
ደሊላ ትዋረዳለች
ደሊላ ጌታ ይበቀላታል
ደሊላ ትዋረዳለች
ደሊላ ሥራዋ ይፈርሳል
ደሙ በግንባሩ ሆኖ በመቃኑ
እንዳይነካ እምላክ ከእርሱ ጋራ ነው ለካ (፪x)
ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (፬x)
ዘላለም ድንቅ ነህ
ዘላለም ዕጹብ ነህ
አመልክሃለሁ ልዩ ነህ
አመልክሃለሁ ግሩም ነህ (፪x)
አቤት ውበትህ
ግርማ ሞገስህ (፪x)
ነበልባል ዓይንህ
አቤት ማርኮኛል አስደንቆኛል (፪x)
ውበትህ ማርኮኛል አስደንቆኛል (፪x)
አምላክነትህ ማርኮኝ እኔን አመልክሃለሁ
ጌትነትህም ወርሶት ልቤን እገዛልሃለሁ (፪x)
ግርማ ሞገስህ ዓይኔን አልፎ ልቤን ነካው
እንዳንተ ያለ አምላክ የለም ለካ (፪x)
አምላክነትህ ማርኮኝ እኔን አመልክሃለሁ
ጌትነትህም ወርሶት ልቤን እገዛልሃለሁ (፪x)
ግርማ ሞገስህ ዓይኔን አልፎ ልቤን ነካው
እንዳንተ ያለ አምላክ የለም ለካ (፪x)