Melihke Album Lyrics

Listen for FREE

 icon telegram, logo, messanger, social, social media Website Icon - Westside Regional Center

ዝናውን ለሰማው እጅግ ያስፈራል
ባለዝና እንደሱ ከየት ይገኛል
በዘመናት መሃል ይታወቃል
ብቻውን የበላይ ሆኖ ይኖራል

እግዚአብሔር /4

እግዚአብሔርን ከእኔ ጋራ
ታላቅ አርጉት ዝናው ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ/2
በምድር ሁሉ ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ
በአለም ሁሉ ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ

አንጎዳጎደ ልኡል ቃሉን ሰጠ
በክብሩ ሲቆም ምድርን አናወጠ
የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ
የጥንትም ኮረብቶች ወዲያ ፈራረሱ
ከሚንቦገቦገው ፀዳል የተነሳ
ፍላፆች ከወጡበት ብርሃን የተነሳ
ጨረቃ እና ፀሃይ በቦታቸው ቆሙ
በክብሩ ነፀብራቅ እየተደመሙ

ክብሩ ሰማያትን ሁሉ የሸፈነ
ስሙም በምድር የተመሰገነ
ለታላቅነቱ ፍፃሜ የሌለው
በዘመናት መሃል እርጅና የማያውቀው
ከዋክብት ታዘዙ በህዋ አበሩ
በአፍንጫው እስትንፋስ ውሆች ተከመሩ
ትልቅ የሚለው ቃል ፍፁም የማይገልፀው
እጅጉን ያፈራል ዝናውን ለሰማው

የክብር ንጉስ ሆይ እንዴት ታላቅ ነህ
ከዙፋንህ ስር በእውነት በመንፈስ ልስገድልህ

ከሰው ልጆች ይልቅ ያማረ ውበትህ
የፀጋ ቃል ሁሌ ያፈሳል ከንፈርህ
አይኖቼ አይተውህ
ፈዘዙ በክብርህ /2

ማን ሊመስልህ
አረ ማን ሊያክልህ
አንተ እኮ ከአማልክት ትለያለህ
ውዴ ከአእላፋት ትበልጣለህ

ፊትህ እንደ ፀሃይ በሃይል ያበራል
እንደ ብዙ ውሆች ድምፅህም ያስፈራል
በግርማህ ተገረሜ
ቀረሁኝ ተደምሜ

ማን ሊመስልህ
አረ ማን ሊያክልህ
አንተ እኮ ከአማልክት ትለያለህ
ውዴ ከአእላፋት ትበልጣለህ

ሃሌሉያ/8

Music Arrangement – Robel Damtew
live Bass Guitar – Didi K. Wolde
live Electric Guitar – Eba Bogale
Background Choirs- Solomon Bula and Rediet Yirgu
Mixing and Mastering – Yabets Yimer (YB)

አንተ ባለህበት በከበረው ስፍራ
ካንተ ጋራ ልኖር ስምህን እንድጠራ
እድሉን አገኘው በቤትህ ልቀድስ
እጥፍ ልስገድልህ ነፍሴን ፊትህ ላፍስስ
እንዴት መታደል ነው ስምህን መጥራቱ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ማለቱ
የተመረጠ ስም ከስም ሁሉ በላይ
አይኔን አድርጎታል ካንተ ሌላ እንዳላይ

የህይወቴ ኢየሱስ ጌታ ነህ
ኢየሱስ የኑሮዬ ኢየሱስ ንጉስ ነህ
ኢየሱስ መአዛህን ኢየሱስ ስወደው
ኢየሱስ መገኘትህ ኢየሱስ ህይወቴ ነው

ኢየሱስ ኢየሱስ ወደድኩህ
ከእልፍ ከአእላፋት መረጥኩህ
ውዴ ከእንቁ ትበልጣለህ
ከማር ወለላ ትጣፍጣለህ
እረ እንዴት እድለኛ ነኝ
በፊትህ ሞገስን አገኘሁኝ
የኔ ብቻ አይበቃም ዝማሬ
ይገዛልህ ዘር ማንዘሬ

የቤትህ ስርአት በሚደረግበት
ህዝቡም መላእክቱም ቅዱስ በሚሉበት
እድሉን አገኘው ዘላለም ላመልክህ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያልኩ ከቅዱሳንህ
እንዴት መታደል ነው ዘላለም ማምለኬ
ጎንበስ ቀና እያልኩ ፊትህ ተንበርክኬ
በማይነገር ክብር በሚደነቅ ብርሃን
ላይህ ጉዋጉቻለው ውዴ ኢየሱስ አንተን

ኢየሱስ ሙሽራዬ ኢየሱስ ቶሎ ና
ኢየሱስ መናፈቄ ኢየሱስ በዝትዋልና
ኢየሱስ ማዶ ማዶ ኢየሱስ ማዶ እያየው
ኢየሱስ አማትሬ ኢየሱስ እጠብቅሃለው

Music Arrangement – Ermias Molla
Live Bass – Dawit kumera(Didi)
Live acoustic and electric guitar – kalab tekil
Choir Director – Ermias Molla
Choir Team – Oneway Production
Mixing & Mastering – Yabets Yimer( YB)

በእኔ ፈንታ ተተክቶ
ወጥቻለው እስሬ ተፈቶ
በሃጥያቴ ምክንያት እንዳልቀጣ
ክርስቶስ እየሱስ ክብሩን ትቶ መጣ

እዳዬንም እሱ ከፍሎልኛል
ነፃ ሰው ነኝ ዋሴ ሆኖልኛል
አድራሻዬ በሰማዩ ስፍራ
አድርጎታል ከእግዚአብሔር ጋራ

ኩነኔ የለብኝም አሁን ኩነኔ
ነፃ ወጥቻለው በመድህኔ

ምንም ሳላደርግ ምንም ሳልስራ
በአብ ቀኝ ተቀመጥኩ ከእየሱሴ ጋራ
ምንም ሳልከፍል ያለምንም ዋጋ
የዘላለም ህይወት አገኘው በፀጋ
እንዲሁ በፀጋ/2
የዘላለም ህይወት አገኘው በፀጋ

ራሱ ሰጠ ለኔ ሊገረፍ
አንድም ጅራፍ በኔ ላይ እንዳያርፍ
መራራውን ፅዋ እንዳልጠጣው
አበሳዬ ወስዶ ጨረሰው

የአለምን ሃጥያት ሚያስወግደው
የእግዚአብሔር በግ በደሌን ሰቀለው
በራሱ ደም ይዞኝ አብ ጋር ገባ
አለበሰኝ ፀጋውን እንደ ካባ

Music Arrangement- Ermias Senbeto
Guitar…Ermias Tadele
Backup Singers… Bereket Zewdu, Yosef Jano
Mixing and Mastering – Yabets Yimer (YB)

ሁልግዜ ትክክል ነህ
ሁልግዜ አዋቂ ነህ
ሁልግዜ ትክክል ነህ
ሁልግዜ አዋቂ ነህ
ካንተ ጋር እስማማለው
ፈቃድህ ይሁን እላለው

ፈቃድህ ሁሌም ነው መልካም
ስትሰራ አትሳሳትም
ቢገባኝም ባይገባኝም
ሳታውቀው የሚሆን የለም

ከታዘዝኩት ትእዛዝ
በምድራዊው ሃሳብ እንዳልያዝ
ከታዘዝኩት ትእዛዝ
በምድራዊው ኑሮ እንዳልያዝ
አይኖቼን አቀናለው
በላይ ያለውን እሻለው

ሳስበው በላይ ያለውን
ዘላለም የምኖረውን
ሳስበው በላይ ያለውን
አምላኬ ያዘጋጀውን
አይን ያላየው ጆሮ ያልሰማው
ክብር ነው ያለው /3
አይን ያላየው ክብር ነው ያለው
ጆሮ ያልሰማው ክብር ነው ያለው

ከታዘዝኩት ትእዛዝ
በምድራዊው ሃሳብ እንዳልያዝ
ከታዘዝኩት ትእዛዝ
በምድራዊው ኑሮ እንዳልያዝ
አይኖቼን አቀናለው
በላይ ያለውን እሻለው

ሳስበው በላይ ያለውን
በአብቀኝ የተቀመጠውን
ሳስበው በላይ በላይ ያለውን
ሙሽራዬ የሚወስደኝን
አየዋለው አገኘዋለው
ደስታዬ እርሱ ነው
ፍስሃዬ ነው
ዘላለሜ ነው
እየሱሴ ነው

Guest singer – Yabets Yimer (YB)
Music Arrangement/ Mixing and Mastering – Yabets Yimer (YB)
Live Guitar – Eba Bogale
Choir Director – Ermias Molla
Choir Team – Oneway Production

የታመነህ ሰው እንደንጋት ብርሃን ህይወቱ ይደምቃል
የታመነህ ሰው ሙሉ ቀን እኪሆን ጨምሮ ያበራል
አንተን ያመነ አይፈራ አይደነግጥ በለሊቱ
አንተን ያመነ ቃልህ ይሆንለታል ለእግሩ መብራቱ

የሚጤሰውን ጥዋፍ አታጠፋምና
ቅጥቅጡን ሸንበቆ አትሰብርምና
ስለዚህ አይኔን ወዳንተ ላቅና
ስለዚህ ልቤን ባንተ ላፅና

አይኔን አቀናለሁ
ልቤን አፀናለሁ
አንተኑ/2 እታመንሃለው
አንተኑ/2 እደገፍሃለው
እግዚአብሔር አለቴ እታመንሃለው
አምባ መድሃኒቴ እደገፍሃለው

የታመነህ ሰው በወንዝ ዳር እንዳለ ዛፍ ይሆናል
የታመነህ ሰው ሁሌ ይለመልማል ሁሌም ያፈራል
አንተን ያመነ ዙሪያው ደረቅ ቢሆን ምድረበዳ
አንተን ያመነ ለሌላው ይተርፋል አይሆንም ባለ እዳ

የታመነህ ሰው ቃልህን ይሰማል ደግሞም ያደርጋል
የታመነህ ሰው በፀናው አለት ላይ ቤቱን ይሰራል
አንተን ያመነ ዝናብ ጎርፍ ንፋሱ መጥቶ ቢገፋው
አንተን ያመነ አልፎት ይሄዳል እንጂ ጫፉን አ

Music Arrangement – Destahun Jacob
Saxophone – Zerihun belete
Live E-Guitar – kalab tekil
Mixing and Mastering – Yabets Yimer (YB)

ክንዳችሁ አይላላ
ጉልበታችሁ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ
የናዝሬቱ እየሱስ አለ ከእኛ ጋራ

ከግብፅ ከባርነት ከፈርዖን ብዛት
ህዝቡን ያሳረፈ ከጭንቀት ከፍርሃት
በእሳት በደመና በቀን ሌት የመራ
ያው የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ
መንገዱ እጅግ እሩቅ ቢመስል ሚከብድ ማያልቅ
የአለም ኑሮ ፈተና ቢሆንም ትንቅንቅ
ከእኛ ጋራ ያለው አለምን አሸንፏል
እስከ ፅዮን ድረስ በድል ይመራናል

ክንዳችሁ አይላላ
ጉልበታችሁ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ
አማኑኤል እርሱ አለ ከእኛ ጋራ

ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የወጡ ወደ ሰልፉ
የአንበሶችን አፍ ዘጉ የእሳትን ሃይል አጠፉ
በቅንም ፈረዱ መንግስታቱን ድል ነሱ
አለምን ኮነኑ ጣኦትን አፈረሱ
ዛሬም ከበውናል እነርሱ እንደደመና
ክንዳችን እንዳይላላ ጉልበታችን ይፅና
የፃድቅ ጉልበቱ ነውና እምነቱ
ቅዱሳን ካህናቱ እልፍ በሉ በርቱ

ክንዳችሁ አይላላ
ጉልበታችሁ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ
ተስፋውን የሰጠው አለ ከእኛ ጋራ

ሃይልን በሚሰጠን ሁሉን እንችላለን
በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን

ክንዳችን ይበርታ ጉልበታችን ይፅና
አምላካችን ብርቱ ሁሉን ቻይ ነውና

Kindachu Aylala
Music arrangement/ Mixing and Mastering- Yabets Yimer (YB)
Live E-Guitar – Natnael Desalegn
Choir Director – Ermias Molla
Choir Team – Oneway Production

ገና ሰማይ እና ምድር ሳይፈጠር
ገና አማልክት የሚባል ሌላ ሳይኖር
ብቻህን በክብር ዙፋን ላይ ተቀምጠህ
ትመለካለህ

ገና ሰማይ እና ምድር ሳይታሰቡ
ገና ነፋሳት ሳይወጡ ከመዛግቡ
በአእላፋት መላእክት ቀን ከሌት ተከበህ
ትመለካለህ/ 8x

ክብር የሚለው ቃል ሌላ ሳይከብርበት
አንተ ክብር ጠግበህ ዘላለም ኖርክበት
ክብር የሚለው ቃል ማንም ሳይከብርበት
አንተ ክብርን ጠግበህ ዘላለም ኖርክበት
ክብር ማለት የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመርያ የታወቀው ባንተ ነው

እናመልክሃለን እግዚአብሔር

Music arrangement- Dawit Getachew
Live Drum – Mintesinot Biniyam
Live Bass Guitar – Beteab Kassa
Live Electric Guitar – Abenezer Dawit
Backup Choir arrangement – Solomon Bula, Rediet Yirgu
Mixing and Mastering – Yabtse Yimer (YB)

ነፋሱ ቢነፍስ ወጀቡ ቢያጉዋራ
በበዛው ሰላምህ አለህ ከኔ ጋራ
አለም ብትናወት ማእበሉ ቢበዛ
ነፍሴ እርፍ አለች በፍቅርህ ተይዛ

የዘላለሜ ነህ ሁሉ ሲቀር ኃላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ

መልህቄ/2x/
ያዝከኝ ኢየሱሴ

የፍቅርህ ሰንሰለት አጥብቆ ይዞኛል
እኔ ብደክምበት መቼ ይተወኛል
በሞትህ ወደ ታች ወርደህ መልህቄ ያዝከኝ
ልዩ ፍጥረት ቢሆን ሞትም እንዳይለኝ

እንደ ነፍስ መልህቅ በሆነ ተስፋ
እርግጥ እና ፅኑ መቼም የማይጠፋ
በዚህኛው ቢሆን በወዲያኛው አለም
ጥብቅ አርገህ ያዝከኝ እስከለዘላለም

አምናለው ዛሬም በዚህ አለህ
አምናለው ዛሬም ትሰራለህ

Music Arrangement – Dawit Getachew
Live Electric Guitar – Abenezer Dawit
Mixing and Mastering – Yabets Yimer(YB)

አንተ ብቻነህ ፈጣሪ ብቻህን ፈጣሪ
ጀማሪ ፈጣሪ የሁሉ ፈጣሪ

ይሁን ይሁን ብለህ
ፍጥረታትን በቃልህ ፈጠርህ
መጥቶልሃል ያልነበረው
አቤት ብሎሃል የማይሰማው
አንተ ያልከው የቀረ የለም
ፀንቶልሃል በቃልህ ሁሉም

የሰማይ ምድሩ የውቅያኖሱ
የሚበሩ ሚንቀሳቀሱ
ፈጥረህ ብቻ መቼ ተውካቸው
መልካም ነው ብለህ ባርካቸው
የህያዋን ምንጭ ህይወት ጀማሪ
የግኡዛን ደግሞ ፈጣሪ

ማን ነበረና ሊያማክርህ
አንተ ብቻህን ሁሉን ፈጣሪ
ያላማካሪ ብቻህን ሰሪ
እግዚአብሔር ነህ ሁሉን ፈጣሪ

ደግሜ ደግሜ ስምህን ባወድስ
የህይወት ቃል ያለህ የናዝሬቱ ኢየሱስ
አጥንት እና ስጋዬ አካላቴ ሁሉ
ደግመህ ደግመህ ጥራልን አሁንም ይላሉ

ኢየሱስ/3
ኢየሱስ/2 ኢየሱሴ
ሁልግዜ ባወራህ አትጠግብም ነፍሴ

አትጠገብም ቢጠሩህ ቢጠሩህ አትጠገብም
አትጠገብም ቢያመልኩህ ቢያመልኩህ አትጠገብም
አትጠገብም ቢወዱህ ቢውውዱ አትጠገብም
አትጠገብም ቢያፈቅሩህ ቢያፈቅሩህ አትጠገብም

በማለዳ በቀን በለሊት ብጠራህ
እጅጉን ጣፋጭ ነው ኢየሱሴ ስምህ
እንደሚፈስ ዘይት በውስጤ ይፈሳል
መአዛውም ያውዳል ባለህበት ያስቀራል

አትጠገብም ቢጠሩህ ቢጠሩህ አትጠገብም
አትጠገብም ቢያመልኩህ ቢያመልኩህ አትጠገብም
አትጠገብም ቢሰሙህ ቢሰሙህ አትጠገብም
አትጠገብም ቢያወሩህ ቢያወሩህ አትጠገብም

አትጠገብም/3
አትለመድም/3

Original music composition Dawit Lemi
Music arrangement- Muzmure Dawit
Live Guitar – Kalab Tekil
Mixing & Mastering – Yabets Yimer(YB)

ሁሌ
ሁሌም ላመስግንህ ሁሌ

አመስግኜህ አልጠግብም
ባርኬህ አልረካም
አድንቄህ አይወጣልኝ
ለውለታህ ምላሽ ባይሆንልኝ
አመሰግናለው /4
ከፍ አደርግሃለው /4
አመሰግናለው
አጨበጭባለው

ድግሱን ደግሼ የምስጋና
በከበሮ በመሰንቆ በበገና
ብላልኝ ጠጣልኝ እልሃለው
በቤቴ ሁልግዜ ምስጋና ነው

ምስጋና ምስጋና ለእየሱስ ምስጋና
በከበሮ በበገና ለእየሱስ ምስጋና

አመስግኜህ አልጠግብም
ባርኬህ አልረካም
አድንቄህ አይወጣልኝ
ለውለታህ ምላሽ ባይሆንልኝ
አመሰግናለው /4
ከፍ አደርግሃለው /4
አመሰግናለው
አጨበጭባለው

አንተ የከበርከው እንግዳዬ
ደስ ይበልህ ሙሉ ነው ገበታዬ
ሁሉንም ውሰደው ለአንተ ነው
ሌላ እንግዳ የለኝ ምጠብቀው/ የምሰጠው

ምስጋና ምስጋና ለእየሱስ ምስጋና
በከበሮ በበገና ለእየሱስ ምስጋና

አመስግኜህ አልጠግብም
ባርኬህ አልረካም
አድንቄህ አይወጣልኝ
ለውለታህ ምላሽ ባይሆንልኝ
አመሰግናለው /4
እልልም እላለው
ከፍ አደርግሃለው
አጨበጭባለው

Music arrangement/ Mixing and Mastering – Yabets Yimer (YB)
Live Drum – Vince Oppong
Live Bass – Joel Nti-Amankwah (Big-J)
Live E-Guitar – Natnael Desalegn
Choir Director – Ermias Molla
Choir Team – Oneway Production
Saxphone – Samson Workineh
Trombone- Yesak Dawit
Trumpet-Bereket Telahun

አርነት አለ አንተ ባለህበት
መፈታት አለ አንተ ባለህበት

ስምህ ሲጠራ ኢየሱስ ሲባል
ደዌ ይፈወሳል አጋንንት ይርቃል/ይሸሻል
ያዘነው ይፅናናል በደስታ ይሞላል
የስምህ ጉልበት ይህንን ያደርጋል

ልብን የምትፈውስ
ነፍስን የምትመልስ
ሰባራውን የምትጠኝ
አንተ ብቻ ነህ ኢየሱስ

ኢየሱስ/4ስምህ ሲጠራ ኢየሱስ ሲባል
ጥያቄ ይመለሳል ቁዋጠሮ ይፈታል
ደካማው ይበረታል ታምራት ይሆናል
የስምህ ጉልበት ይህንን ያደርጋል

የጌቶች ጌታ ነው
እየሱስ የማመልከው
መፅሃፉን ወስዶ ማህተሙን የፈታ
የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ
ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ
ገናናው ኢየሱስ ብቻውን ድል ነሳ

ከእርሱ ጋራ ሊሰለፉ
የወደዱ ሁሉ አለፉ
ኢየሱስ ግን አለ በዙፋኑ
በማእረጉ በስልጣኑ

የለም የለም
እንደርሱ ያለ የለም
በሰማይ የለም በምድር የለም/2

የከፈተውን ማን ይዘጋዋል
የዘጋውን ማን ይከፍተዋል
ተውባይ ከልካይ አንድ እንኩዋን የሌለው
ቁልፉ እሱ እጅ ብቻ ነው

ከዘላለም እስከ ዘላለም
ህያው ሆኖ የሚኖር እንደርሱ የለም
ከነገድ ከቁዋንቁ ህዝቡን የዋጀው
የታርደው በግ እርሱ ብቻ ነው

Music Arrangement – Abenzer Tafesse
Live Bass Guitar – Bereket Abebe
Live Electric Guitar -Abenezer Dawit
Saxophone – Zerihun belete
Back up Choir – Kabowd Worship choir
Mix & Mastering – Yabets Yimer (YB)

አንተ የእኔ ነህ/2
ማንም የማይወስድህ

አለኝ የምለው የራሴ
እርግጠኛ የምሆነው በመንፈሴ
አንተን ብቻ አንተን ብቻ ነው
የራሴ የግሌ የምለው

እርግጠኛ እርግጠኛ ነኝ/3
እኔን ካንተ ማንም እንዳይለየኝ

ሃብት ወዳጅ ከእኔ ጋር ያሉ
በምድር ላይ እዚሁ ይቀራሉ
ለዘላለም ያገኘሁህ ሃብቴ
መንፈስ ቅዱስ ህይወቴ ነህ ርስቴ

እርግጠኛ እርግጠኛ ነኝ/3
እኔን ካንተ ማንም እንዳይለየኝ

የማላይህ የማልዳስስህ
ከማየው በላይ ግን ደግሞ የማምንህ
ከእስትንፋሴ ይልቅ ቅርብ ነህ
መንፈስ ቅዱስ የልቤ ወዳጅ ነህ

እርግጠኛ እርግጠኛ ነኝ/3
እኔን ካንተ ማንም እንዳይለየኝ

Music Arrangement – Dawit Getachew
Live Drum – Mintesinot Biniyam
Live Bass Guitar – Beteab Kassa
Live Electric Guitar – Abenezer Dawit
Backup Choir arrangement –
Solomon Bula, Rediet Yirgu
Mixing and Mastering – Yabtse Yimer(YB)

እግዚአብሔር ባይራራልኝ
ልጁን ልኮ ባይታደገኝ
የጠላት ሴራ ወጥመድ ዘርግቶብኝ
በሙታን ሰፈር እዛው ላይ በቀረሁኝ

ግን አልተሳካም አልሆነለትም
ነፍሴ ከቶ አላገኛትም
በክርስቶስ በተሰራው ስራ
አመለጠች እንደወፍ በራ

አመለጠች/4
ነፍሴ እንደወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች

በርራ በርራ እንደ ወፍ በርራ /2
አመለጠች በርራ /2
በክርስቶስ ስራ
አመለጠች በርራ
በመስቀል ላይ ስራ
አመለጠች በርራ

አዳኙ በስውር ወጥመድ አስቀመጠ
ከአሁን አሁን ያዘልኝ ሲል አይኑ እንዳፈጠጠ
አዳኜ ሲመጣ ወጥመዱን ሲረግጠው
ነፍሴን አስመልጦ ቀንበሩን ሰባበረው /4

እንዲህን ነው ያመለጠችው ነፍሴ/2
እንደወፍ አመለጠች ነፍሴ /2
በረረች አመለጠች ነፍሴ /2
በአዳኝዋ በኢየሱሴ/4
በኢየሱሴ

ሞትና ሲኦል አንድ ላይ ተስማምተው
ዘላለሜን ሊያደርጉት በድቅድቅ ጨለማው
የትንሳኤው ጉልበት ሞትን ራሱን ገድሎት
መውጊያውን ሰባብሮ ነፍሴ አስመለጣት/4

እንዲህን ነው ያመለጠችው ነፍሴ/2
እንደወፍ አመለጠች ነፍሴ /2
በረረች አመለጠች ነፍሴ /2
በአዳኝዋ በኢየሱሴ/4
በኢየሱሴ

Music arrangement/ Mixing and Mastering- Yabets Yimer (YB)
Live Bass – Kirubel Tesfaye
Live E-Guitar – Abenezer Dawit
Saxphone – Samson Workineh
Back up Choir – Kabowd Worship choir