Misale Yeleleh Lyrics

ኦሆሆሆ (፫x)

እግዚአብሔር ብቻ ግርማህ አስፈሪ
የሌለህ አቻ ተወዳዳሪ ሆሆ ተወዳዳሪ
በትረ መንግሥትህ በዓለም የታወቀ
እንዳንተ ማነው ሁሉን የበለጠ
ሆሆ ከሁሉም የላቀ (፪x)

ልዑል ሰማይ ዙፋንህ
ልዑል ምድር መርገጫህ
ልዑል ለግዛትህ ወሰን
ልዑል የሌለህ ዳርቻ
ልዑል ከፍ ካለው በላይ
ልዑል ከፍ ያለው ዙፋንህ
አምልኮና ስግደት ይሁንልህ (፪x)

ይብዛልህ ምሥጋናዬ ላብዛልህ ዕልልታዬ
በዘመኔ ሁሉ ሥራዬ ይኸው
ምሥጋናዬ ዙፋንህን ይክበበው
አምልኮዬ ክቡር ሥምክን ያድምቀው (፪x)

ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ ቢሰበሰብ ፍጥረት
የሰማይ ሰራዊት እልፍ ጊዜ አላፋት
ሁሉም ተሰብሰቦ ስለ አንተ ቢያወራ
ሊገልፅህ ቢሞክር በተራ በተራ
ምሳሌ የሌለህ ነህ ምሳሌ የሌለህ
ምሳሌ የሌለህ ነህ ምሳሌ የሌለህ (፪x)

ልዑል ሰማይ ዙፋንህ
ልዑል ምድር መርገጫህ
ልዑል ለገዛትህ ወሰን
ልዑል የሌለህ ዳርቻ
ልዑል ለትልቅነትህ
ልዑል ምሳሌ የሌለህ
አምልኮና ስግደት ይሁንልህ

ይብዛልህ ምሥጋናዬ ላብዛልህ ዕልልታዬ
በዘመኔ ሁሉ ሥራዬ ይኸው
ምሥጋናዬ ዙፋንህን ይክበበው
አምልኮዬ ክቡር ሥምህን ያድምቀው (፪x)

አቻ አጣሁልህ ወደር አጣሁልህ
መሳይ አጣሁልህ እኩያ አጣሁልህ
አቻ አጣሁልህ ወደር አጣሁልህ
መሳይ አጣሁልህ እኩያ አጣሁልህ
በሰማይ በምድር የለም የሚመስልሁ (፬x)

አቻ አጣሁልህ ወደር አጣሁልህ
መሳይ አጣሁልህ እኩያ አጣሁልህ (፪x)

በሰማይ በምድር የለም የሚመስልህ (፬x)

አቻ አጣሁልህ ወደር አጣሁልህ
መሳይ አጣሁልህ እኩያ አጣሁልህ (፪x)

በሰማይ በምድር የለም የሚመስልህ (፬x)

አንተ የከበርክበት ከፍ ከፍ ያልክበት
የላቀ ሥልጣንህ ማነው የደረሰበት
ወልድ የተረከህ ሆይ ስለ ማንነትህ
ፅድቅ ነው ዙፋንህ ብርሃን አልባሳትህ
ምሳሌ የሌለህ ነህ ምሳሌ የሌለህ
ምሳሌ የሌለህ ነህ ምሳሌ የሌለህ (፪x)

ልዑል ሰማይ ዙፋንህ
ልዑል ምድር መርገጫህ
ልዑል ለገዛትህ ወሰን
ልዑል የሌለህ ዳርቻ
ልዑል ለትልቅነትህ
ልዑል ምሳሌ የሌለህ
አምልኮና ስግደት ይሁንልህ

ይብዛልህ ምሥጋናዬ ላብዛልህ ዕልልታዬ
በዘመኔ ሁሉ ሥራዬ ይኸው
ምሥጋናዬ ዙፋንህን ይክበበው
አምልኮዬ ክቡር ስምህን ያድምቀው (፪x)

ከማንም ጋር አላወዳድርህም
ከማንም ጋር እኩያ አላደርግህም (፪x)

ለጌታዎቹ ጌታ ነህ
ለነገሥታቱም ንጉሥ ነህ
ለኃያላኑም ኃያል ነህ
እግዚአብሔር ልዩ ነህ

ከዘለዓለም ዘለዓለም በፊት ብቻህን የነበርከው
ከዘለዓለም ዘለዓለም በኋላ ብቻህን የምትኖረው
ፍጥረት ቢያመልክ ባያመልክህ ቢዘል ባይሰግድልህ
ከክብርህ ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጐድልብህ
ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጐድልብህ (፪x)

እውነት ነው እኔ ዝም ብል ድንጋዮች ይናገሩልሃል
እጅ እግሬን አጥፌ ብቀመጥ ኮረብቶች ይዘሉልሃል
ወንዞች ያጨበጭቡልሃል አእዋፋት ይዘምሩልሃል
ስለጐደለህ አይደለም እኔ የምጨምረው
ስላነሰህም አይደለም እኔ የማበዛው
ስለሚገባህና ስለተገባህ ነው (፪x)

የተለየ ነው አምላክነት ንግስናህ
የተለየ ነው ገናናነትህ ዝናህ
የተለየ ነው መቀመጫህ ዙፋንህ
የተለየ ነው ማስፈራቱ የክብርህ

አልፋ ነህ ኦሜጋ መጀመሪያ መጨረሻ
አልፋ ነህ (አልፋ ነህ) ኦሜጋ (ኦሜጋ)
መጀመሪያ (መጀመሪያ) መጨረሻ (መጨረሻ)

አልፋ ነህ ኦሜጋ መጀመሪያ መጨረሻ
አልፋ ነህ (አልፋ ነህ አልፋ ነህ) ኦሜጋ (ኦሜጋ ኦሜጋ)
መጀመሪያ (መጀመሪያ መጀመሪያ) መጨረሻ (መጨረሻ)

አልፋ ኦሜጋ
ኦሜጋ ነህ መጨረሻ
ሁሉን የምትገዛ ጌታ

አዝ፦ ተስፋ አለው ፊትህን ሳየው
በረታሁ ፊትህን ሳየው
ደስታ አለው ፊትህን ሳየው
ተጽናናሁ ፊትህን ሳየው (፬x)

አቅም አጥቼ ጉልበት ሲላላ
እምነቴ ጠፍቶ ሳይ ወደኋላ (፪x)
አሁንስ ተስፋዬ ማነው ብዬ
ከአፌ ሳልጨርስ መጣህ አባብዬ

ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብከኝና
ላመሰግንህ ቆምኩ እንደገና (፪x)
ላመሰግንህ እንደገና ላመሰግንህ ቆምኩ እንደገና
ላመሰግንህ እንደገና ላመሰግንህ ቆምኩ እንደገና

አዝ፦ ተስፋ አለው ፊትህን ሳየው
በረታሁ ፊትህን ሳየው
ደስታ አለው ፊትህን ሳየው
ተጽናናሁ ፊትህን ሳየው (፪x)

በመተማመን የጠበቀህ ሰው
የሚጐበኝበት ቀኑ ቢርቀው (፪x)
በምትዘገይ ተስፋ እንዳያዝን ልቡ
ፈጥነህ ትደርሳለህ ታማኝ ነህ አምላኩ

ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብከኝና
ላመሰግንህ ቆምኩ እንደገና (፪x)
ላመሰግንህ እንደገና ላመሰግንህ ቆምኩ እንደገና
ላመሰግንህ እንደገና ላመሰግንህ ቆምኩ እንደገና

አዝ፦ ተስፋ አለው ፊትህን ሳየው
በረታሁ ፊትህን ሳየው
ደስታ አለው ፊትህን ሳየው
ተጽናናሁ ፊትህን ሳየው (፬x)

ዓይኖቼን ወደተራሮች ባቀና
ረዳቴ ይመጣል ብዬ ደጅን ብጠና
ግን ተራራዎች መልስን ሰጡኝ በዝምታቸው
ሚስጥሩ ገባኝ እነርሱም እርዳታ እንደሚያሻቸው

ከታራራውም ላይ አሻቅቤ ሳይ በላይ በሠማይ
ረድኤቴ መጣ እይተራመደ በደመናት ላይ
እንደ እግዚአብሄር ያለ ማንም እንደሌለ ይህንን ስላየሁ
የዘለዓለም አምላክ መኖሪያዬ አድርጌዋለሁ (፪x)

እንደተፈታች ሚዳቋ እንደተፈታች
እንደተፈታች እምቦሳ እንደተፈታች
ልውጣ ላይ ልውረድ ታች ነፍሴ ሃሴት ስላረገች
ቧረቀች ፈነደቀች ነፍሴ ሃሴት ስላረገች (፪x)

እስቲ ክበር በሉት ክበር
እስቲ ንገሥ በሉት ንገሥ
ጌታን ክበር በሉት ክበር
ጌታን ንገሥ በሉት ንገሥ
እጅግ ደስ ይለኛል ሥሙ ሲወደስ
ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ (፪x)

ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ
ክበር ክበር ክበር
ንገሥ ንገሥ ንገሥ
ይክበር ይክበር ይክበር
ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ

በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ቀርቶ
እርሷንም ተራምዶ ውጦ ሊያስቀረኝ እጅጉን ጓግቶ
በጠላትም ሰፈር በቃ ሽንፈቴ ተረጋገጠ
ግን ረዳቴ መጣ በቅጽበት ነገሩ ተገለበጠ

ሊሰለጥንብኝ ባለው ቀን ጠላቴ ሰለጠንኩበት
ለእኔ በቆፈረው ጉድጓድ እርሱ ተቀበረበት
ድል አድራጊው ጌታ ድል እያደረገ በሰልፉ መሃል
በምሥጋና ነዶ በምርኮ ብዛት ያዘምረኛል/ያዘልለኛል (፪x)

እንደተፈታች ሚዳቋ እንደተፈታች
እንደተፈታች እምቦሳ እንደተፈታች
ልውጣ ላይ ልውረድ ታች ነፍሴ ሃሴት ስላረገች
ቧረቀች ፈነደቀች ነፍሴ ሃሴት ስላረገች (፪x)

እስቲ ክበር በሉት ክበር
እስቲ ንገሥ በሉት ንገሥ
ጌታን ክበር በሉት ክበር
ጌታን ንገሥ በሉት ንገሥ
እጅግ ደስ ይለኛል ሥሙ ሲወደስ
ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ (፪x)

ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ (፫x)
ንገሥ ንገሥ ንገሥ
ይክበር ይክበር ይክበር
ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ

ጌታ ኢየሱስ እውነተኛ ወዳጅ ነህ
ነፍስህን የሰጠህ ስለ እኔ (፪x)

ኧረ ማን አለ እንዳንተ እኔን የወደደ (፪x)

ፍቅርህን ሳስበው ይደንቀኛል
ላወራው ሳልጀምር ቃል ያጥረኛል
በልቤ ተጽፎ ቅዱስ ቃልህ
ሁሌ ያስታውሰኛል ትኩስ ነው ፍቅርህ (፪x)

ከዚህም የሚበልጥ ፍቅር የታለ
እንዳንተ የሚወደኝ ኧረ ማን አለ (፪x)
ማን አለ (፫x)
ማን አለ (፫x)
ማን አለ (፬x)

ፍቅር ማለት እንዳንተ ነው
ወዳጅ ማለት እንዳንተ ነው
አፍቃሪ ማለት እንዳንተ ነው
ወዳጅ ማለት እንዳንተ ነው
ፍቅር ማለት እንዳንተ ነው
አፍቃሪ ማለት እንዳንተ ነው

የፍቅርን ትርጉሙን አስተማርከኝ
እውነተኛ ፍቅር አሳየኀኝ (፪x)

አሃሃ አሃሃ (፬x)
ኢየሱስ ፍቅር ነው (፬x)
ያሽዋ አሃሃ (፬x)
አሃሃ አሃሃ (፬x)
ኢየሱስ ፍቅር ነው (፬x)
የሽዋ አሃሃ (፬x)

ክብር ይሁንለት ለንጉሡ
ወደ ማደሪያው ይግባ ወደመቅደሱ (፪x)
ክበር ክበር ክበር በምሥጋና
እጅግ ለተፈራው ለሆነው ገናና (፪x)
በመቅደሱ ምሥጋናዬን አሰማለሁ በተራዬ
ከሚፈሩት ቅዱሳኑ ጋር እለዋለሁ ክበር
በመቅደሱ ምሥጋናዬን አሰማለሁ በተራዬ
ከሚፈሩት ቅዱሳኑ ጋር እለዋለሁ አምላኬ ክበር

ክበር የእኔ ጌታ ክበር
ክበር ለዘለዓለም ክበር
ክበር ሁልጊዜ ክበር
ክበር ለዘለዓለም ክበር

የምህረት ደጁ ለእኔ ተከፍቶ
አየሁ የንጉሥ ዘንግ ደግሞ ተዘርግቶ
ከጨለማው ገዢ ነጥቆ አውጥቶ
ወደ ፍቅሩ መንግሥት አስገባኝ ጐትቶ (፪x)

ሃሌሉያ አሃ (፬x)
ሃሌሉያ አሃሃ (፬x)

በምህረቱ ገባሁ ማን ሊከለክለኝ
ኢየሱስ ቤዛዬ አዳኝ ስለሆነኝ
ቅዱሱ ባለበት በውስጠኛው ስፍራ
አገልጋይ አደረገኝ ስሙን እንድጠራ (፪x)

ምህረቱ ከቦኛል በቅዱስ ደሙ አንጽቶኛል
ታዲያ ማነው የሚቃወመኝ ኢየሱሴ ካጸደቀኝ
ምህረቱ ከቦኛል በቅዱስ ደሙ አንጽቶኛል
ታዲያ ማነው የሚኮንነኝ ኢየሱሴ ካጸደቀኝ

ሃሌሉያ አሃ (፬x)
ሃሌሉያ አሃሃ (፬x)
ኦሆ ኦሆ ኦሆሆ
ሃሌሉያ አሃሃ (፬x)

የከበረ ከሁሉ የተሻለ
የከበረ ከሁሉ የተሻለ
ሰውነቴ ለአንተ አቀርባለሁ (፪x)
እኔነቴን ለአንተ አቀርባለሁ (፪x)

መሰዊያን ሰራሁ ልሰዋልህ በፊትህ ላቀርበው
ያለኝን በሙሉ ታውቀዋለህ የቱን ነው ምትሻው
እያልኩኝ ስደረድር ምድርና ሞላዋ ለካስ የአንተ ነው
የሚቃጠል መስዋዕት ደስ እንዳያሰኝህ ይህንን ተረዳሁ

ታዲያ እኔም ምኔን ልስጥህ
ምን ሰጥቼ/ሰውቼ ደስ ላሰኝህ
እያልኩኝ ስጠይቅ ቃልህን
ስጠው/ሰዋው አለኝ እራስህን (፪x)

ስለዚህ እራሴን ሕያውና ቅዱስ አድርጌ
ፊትህን ደስ እንዳሰኘሁ ፈቀድኩኝ ልሰዋ ይኸው
ልዩ ጣዕም የመዓዛ ሽታ
ሆኜ ልቅረብ በፊትህ ጎይታ

ከሚቃጠል መስዋዕት ጋራ ወደፊትህ እመጣለሁ
የአምልኮዬ መዓዛ ሽታ ዙፋንህን ይክበበው
በምህረት የተሞላህ ታላቅ አምላክ ነህና
አሁንም አበዛለሁ ከነፍሴ ምሥጋና

ኦ በምሥጋና በዝማሬ እመጣለሁ
ኦሆሆ ወደ ማደሪያህ እገባለሁ (፮x)

ሕይወቴን ሰጥቼ ተከተልኩት
የነፍሴ ጌታ አደረኩት
ለመጪውም ዘመን እጣ ፈንታዬ
ላደርገው ወሰንኩኝ ከለላዬ
መላው እኔነቴን አስገዝቼ
መኖር ጀመርኩኝ ተደስቼ (፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ተጓደደች አምላኳን አግኝታ
ኢየሱስ ኢየሱስ አለች ጠዋት ማታ (፪x)
ኢየሱስ (፬x) ኢየሱስ (፬x)

በተራራዎች ላይ እየዘለለ
በኮረብቶችም ላይ እየተወረወረ
ከፍታን ዝቅታን ሁሉ አልፎ
በመሃል ያለውን አሸንፎ
የውዴ ድምጽ ፈጥኖ ይመጣልኛል
ከአፉ ቃል ነፍሴን ያጠግባታል (፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ተጓደለች አምላኳን አግኝታ
ኢየሱስ ኢየሱስ አለች ጠዋት ማታ (፪x)
ኢየሱስ (፬x) ኢየሱስ (፬x)

ከማር ወለላ ይልቅ ይጣፍጠኛል
ሁሌ ስጠራህ ያስደንቀኛል
የማዐዛው ጠረን ሽታው አውዶኝ
በእርሱ ተስቤ ቤቱ ቀረሁኝ (፪x)

አገልጋይ ሆንኩኝ

ኢየሱስ (፬x) ኢየሱስ (፬x) ኢየሱስ (፬x)

የውሃውን ማዕበል ወጀቡን ሚገስጸው
በአንዲት ቃል ብቻ ግዑዙን የሚያዘው
በድንቅ ተዓምራቱን ልጆቹን የሚስደንቅ
በተለቀባቸው ላይ ሆኖ የሚታይ ትልቅ

(ጌታ እኮ ነው) ጌታ
(ጌታ እኮ ነው) የእኔ ጌታ
(ጌታ እኮ ነው) ጌታ ሁሉንም የረታ (፪x)

አውራቂስ ተነስቶ መርከቢቱን ቢመታ
እንድናለን የሚል አንድ ተስፋ ቢታጣ
ጭንቀቱ ሲበዛ በንፋሱ ብርታት
የማዕበሉ ጌታ እርሱ ነው የእኔ አለኝታ

ስለዚህ ልቤ በማዕበሉ ስላልተሸበረ
በሳንቃ በስብርባሪ ተሻገረ አምላክ የሚያውቁት
ይበረታልና አልያዝም እደርሳለሁ
ወደአየልኝ ገና (ገና)
እሄዳለሁ (ገና) አየዋለሁ (ገና)
እደርሳለሁ (ገና) እይዘዋለሁ (ገና)
ገና ገና (ገና) ገና ገና (ገና)
ክብሩ ገና (ገና) መቼ አየና (ገና)
ገና ገና (ገና) ገና ገና (ገና)
ክብሩ ገና (ገና) መቼ አየና

እርሱ ብቻውን ተዓምራት አድርጊ ነው
በውኃ ላይ ተራምዶ የሚያራምድ ነው (፪x)
እርሱ ብቻውን ተዓምራት አድርጊ ነው
በውኃ ላይ ተራምዶ የሚያራምድ ነው (፬x)

የውሃውን ማዕበል ወጀቡን ሚገስጸው
በአንዲት ቃል ብቻ ግዑዙን የሚያዘው
በድንቅ ተዐምራቱን ልጆቹን የሚስደንቅ
በተለቀባቸው ላይ ሆኖ የሚታይ ትልቅ

(ጌታ እኮ ነው) ጌታ
(ጌታ እኮ ነው) የእኔ ጌታ
(ጌታ እኮ ነው) ጌታ ሁሉንም የረታ (፪x)

የማዕበሉን ብርታት ፀጥ ያደረገው
የንፋሱን ጉልበት በቃሉ ያዘዘው
ተራምዶ የሚያራምድ በአቃተኝ ነገር ላይ
እኔ የማመልከው እርሱ ነው ኤልሻዳይ

ስለዚህ ልቤ በማዕበሉ ስላልተሸበረ
በሳንቃ በስብርባሪ ተሻገረ አምላክ የሚያውቁት
ይበረታልና አልያዝም እደርሳለሁ
ወደአየልኝ ገና (ገና)
እሄዳለሁ (ገና) አየዋለሁ (ገና)
እደርሳለሁ (ገና) እይዘዋለሁ (ገና)
ገና ገና (ገና) ገና ገና (ገና)
ክብሩ ገና (ገና) መቼ አየና (ገና)
ገና ገና (ገና) ገና ገና (ገና)
ክብሩ ገና (ገና) መቼ አየና

እርሱ ብቻውን ተዓምራት አድርጊ ነው
በውኃ ላይ ተራምዶ የሚያራምድ ነው (፪x)
እርሱ ብቻውን ተዓምራት አድርጊ ነው
በውኃ ላይ ተራምዶ የሚያራምድ ነው (፬x)

ገመድ በአንገቴ ሳይገባ
እጅም ሰንሰለት ሳያስረው
እግሬ እየዘለለ አየተወራጨሁ
ታዲያ የምን እስራት ነው
ታዲያ የምን እስራት ነው

አዝ፦ ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ
እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ
ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ
እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ

ዓይኔ እያየ በሚያልፈው ላይ
እንዳልዘረጋ እጄን መዘዙን ሳላይ (እባክህ እርዳኝ)
እንድጋልብበት ሲያምረኝ ፈረሱ
ልጓም ከሌለው ይቅርብኝ እርሱ (፪x)

አዝ፦ ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ
እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ
ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ
እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ

ከንጉሥ ገበታ ከቃሉም ማዕድ
ሁሌም ማልጠፋ ሆኜ የንጉሥ ልጅ
ምነው መክሳቴ ምነው መመንመኔ
የዓለም ቤዛ ሆነኀኝ መድህኔ (፪x)

ገመድ ከአንገቴ ሸክም ከጫንቃዬ
ይሰበር የእግር ብረቱ
ይቆረጥ ከእጄ ሰንሰለቱ

ፍታልኝ እባክህ ፍታልኝ
ፍታልኝ እስሬን ፍታልኝ
ፍታልኝ እባክህ ፍታልኝ
ፍታልኝ ውዴ ፍታልኝ (፪x)

ፍታልኝ ፍታልኝ
ኢየሱስ እስሬን ፍታልኝ
አባቴ አባቴ ፍታልኝ
ፍታልኝ

ኀጢአተኛውን በፍቅር አይተህ
ከሕያውያን ጋር አንተ ቀላቅለህ
ካረከውማ ስምህን እንዲሸከም
ምን ትባላለህ ክበር ተመስገን
ስምህን እንዲሸከም አንተ ከአደረከው
አቤት ጌታዬ እወድሃለሁ
እወድሃለሁ እወድሃለሁ (፪x)

ሥምህን እንዲሸከም አንተ ከአደረከው
አቤት ጌታዬ ተገርሜያለሁ
ሥምህን እንዲሸከም አንተ ከአደረከው
አቤት ኢየሱስ ወድጄሃለሁ

ኃጢአተኛውን በፍቅር አይተህ
ከሕያውያን ጋር አንተ ቀላቅለህ
ካረከውማ ስምህን እንዲሸከም
ምን ትባላለህ ክበር ተመሥገን
ሥምህን እንዲሸከም አንተ ከአደረከው
አቤት ጌታዬ እወድሃለሁ
እወድሃለሁ እወድሃለሁ (፪x)

ሥምህን እንዲሸከም አንተ ከአደረከው
አቤት ጌታዬ ተገርሜያለሁ
ሥምህን እንዲሸከም አንተ ከአደረከው
አቤት ኢየሱስ ወድጄሃለሁ

ህመም ደዌዬን ተሸከመ
ያለ ኃጢአቱ ተገረፈ
በሰው ሁሉ ተጠላ ተናቀ
እንደጠፋ በግ ተቅበዝባዙን ፍለጋ
ተጨነቀ ተሰቃየ
መስቀል ላይ ዋለ ደሙ ፈሰሰ
በትንሳኤው ሃይል ሕያው አደረገኝ
ከአጋር አስታርቆ ከጻድቃን ማህበር ቀላቀለኝ

ይመሥገን ይመሥገንልኝ (፬x)
ይመሥገን ፣ ይመሥገን ፣ ይመሥገን ፣ ይመሥገን
አዎ ይመሥገን (ይመሥገን)
ይመሥገንልኝ (ይመሥገን)

ጌታ ይመሥገን (ይመሥገን)
ይመሥገንልኝ (ይመሥገን) (፪x)
ሁሌ ይመስገን (ይመስገን)
ይመሥገንልኝ (ይመሥገን)
አዎ ይመሥገን (ይመሥገን)
ይመሥገንልኝ (ይመሥገን) (፫x)

ጌታ ይመሥገን (ይመሥገን)
ይመሥገንልኝ (ይመሥገን) (፪x)
ሁሌ ይመስገን (ይመስገን)
ይመሥገንልኝ (ይመሥገን)

ክፉ ሳይመጣ ከሩቅ አይተህ
ለልጅህ ሚስጥርን ትገልጣለህ
እንዳልጠፋ በንፋስ ማዕበሉ
ትታደገዋለህ ሆነህ መርከቡን

አዋቂ ነህ ሁሉንም አውቀኸዋል
የጥፋትን ውኃ ሰብስበሃል
የሞገዱን መናወጥ ዝም አሰኘህ
ለባሪያህ መልካምን አደረግህ

ብዙ ጐርፍ ተነስቶ ሕይወቴን ሊያጠፋ
ዕንቁዬን ሊያስጥለኝ ሊያስቆርጠኝ ተስፋ
ነፍሴን ያስጨነቀ ያናወጠ መከራ
ቀስ በቀስ እየገፋ አወጣኝ ወደ ተራራ
በእሳት ካልነጠረ ወርቅ እንደማይደምቀው
ያኔ እያስጨነቀኝ ለካ ለበጐ ነው
ያረጀው የደከመው እንደተ በፀጋህ ታድሶ
በዝማሬ ተተካ የትላንቱ ለቅሶ

ሃሌሉያ (፫x)
ለታመነህ ሆነሀዋል መጠለያ
የተመካብህ አመለጠ በአንተ ጉያ

ሃሌሉያ (፫x)
የታመነህ ስንቱ ዳነ በአንተ ጉያ
የተመካብህ ስንቱ ዳነ በአንተ ጉያ
የታመነ አመለጠ በአንተ ጉያ

አባቶች በእምነት አምልከውት አለፉ
ነቢያት አወሩለት መለከትን ነፉ
ሓዋሪያት የሰሙት በዐይናቸው ያዩት
በእጆቻችሀው ዳሰው የመሰከሩለት
መቃብር ፈንቅሎ ሞትን ድል የነሳው
እርሱን በማምለኬ እኔ እንጓደዳለሁ

ከሰማያት በላይ ከፍ ብሎ ያለ
በዘምናት መሃል እጅግ የከበረ
በሃይል በችሎቱ ዝናው የገነነ
በፍጥረት ሁሉ ላይ የተመሰገነ
ይሄ ነው ጌታ ይሄ ነው
ይሄ ነው አምላክ ይሄ ነው (፪x)
እኔ የማመልከው

አዝ፦ የማመልከው ይህ የእኔ ጌታ
የማደንቀው የምሰግድለት
እርሱ ብቻ የአማልክት አምላክ
የማመልከው ይህ የእኔ ጌታ
የማደንቀው የምሰግድለት
እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ

ፀሐይን አቁሞ ጨረቃን ያዘገየ
አሰራሩ ልዩ ከሁሉ የተለየ
ባሕርን እንደግድግዳ እንደክምር ያደረገው
የጥንቱ እግዚአብሔር ዛሬም እግዚአብሔር ነው
ይሄ ነው ጌታ ይሄ ነው
አምላክስ ካሉ እንዲህ ነው
መኖር ካልቀረ እርሱ ነው
ካመለኩ አይቀር እርሱን ነው

አዝ፦ የማመልከው ይህ የእኔ ጌታ
የማደንቀው የምሰግድለት
እርሱ ብቻ የአማልክት አምላክ (፪x)

የአህዛብ አማልክት ጣኦታቶች ናቸው
አይሰሙ አያዩ ቢጠሩ አይሰሟቸው
አምላካቸው ይቀስቀስ ተኝቷል ወይ ሲባል
እኔ የማመልከው በእሳት ይመልሳል
የተነሱበትን ሁሉ ያደቀቀ
በአሸናፊነቱ ግድሉ የታወቀ
ይሄ ነው ጌታ ይሄ ነው
አምላክስ ካሉ እንዲህ ነው
መኖር ካልቀረ እርሱ ነው
ካመለኩ አይቀር እርሱን ነው

አዝ፦ የማመልከው ይህ የእኔ ጌታ
የማደንቀው የምሰግድለት
እርሱ ብቻ የአማልክት አምላክ (፪x)

በሕይወት ዘመኔ አድርጌ ጓደኛ
የልቤን ሳዋይህ ሆነህ ሚስጥረኛ
በየእለቱ ችግሬም በዝቶ ቢበረታ
ሁኒታውን ሳላይ ታመንኩ በአንተ ብቻ
አላፈርኩብህም ዛሬ አኩርተኀኛል
በድካሜ ሁሉ ብርታትን ሰጥተሃል
አክሊሌ ሆነህ በእኔ ላይ ታይተሃል
ታማኝ ነህ ቃልህን ፈጽመሃል

አዝ፦ የዘለዓለም ቃልኪዳን ከእኔ ጋር ያደረግህ
ሆሆሆሆ እንዴት ግሩም ነህ
ጻድቅ አምላክ ነህና ይኀው ቃልህን ፈጸምህ
ሆሆ እንዴት ታማኝ ነህ በእውነት ፍፁም ነህ እንዴት ታማኝ ነህ
እንዴት ታማኝ ነህ በእውነት ፍፁም ነህ
እንዴት ታማኝ ነህ ግሩም ድንቅ ነህ

ሆ እንዴት ታማኝ ነህ
ሆ በእውነት ፍፁም ነህ
ሆ እንዴት ታማኝ ነህ
ሆ ኢየሱስ ግሩም ነህ

ሰው ሰውን ተማምኖ ሁልጊዜ ያፍራል
አንተን ያመነ ሰው ግን ከቶ እንዴት ይወድቃል
ከወንድም ይልቅ የምትጠጋጋ
እውነተኛ ወዳጅ ከቶም ማታሰጋ

የውስጤን አዋቂ የልቤን መርማሪ
ሰባራውን ጠጋኝ አጋሚ አስተማሪ
ቃል ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርህ ሃሳቤን
ታውቀዋለህ ያለውን በልቤ

አዝ፦ የዘለዓለም ቃልኪዳን ከእኔ ጋር ያደረግህ
ሆሆሆሆ እንዴት ግሩም ነህ
ጻድቅ አምላክ ነህና ይኀው ቃልህን ፈጸምህ
ሆሆ እንዴት ታማኝ ነህ በእውነት ፍፁም ነህ እንዴት ታማኝ ነህ
እንዴት ታማኝ ነህ በእውነት ፍፁም ነህ
እንዴት ታማኝ ነህ ግሩም ድንቅ ነህ

ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ
ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ
ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ
ሆሆሆሆሆ (፬x)

አላፈርኩብህም ዛሬ አኩርተኀኛል
በድካሜ ሁሉ ብርታትን ሰጥተሃል
አክሊሌ ሆነህ በእኔ ላይ ታይተሃል
ታማኝ ነህ ቃልህን ፈጽመሃል

አዝ፦ የዘለዓለም ቃልኪዳን ከእኔ ጋር ያደረግህ
ሆሆሆሆ እንዴት ግሩም ነህ
ጻድቅ አምላክ ነህና ይኀው ቃልህን ፈጸምህ
ሆሆ እንዴት ታማኝ ነህ በእውነት ፍፁም ነህ እንዴት ታማኝ ነህ
እንዴት ታማኝ ነህ በእውነት ፍፁም ነህ
እንዴት ታማኝ ነህ ግሩም ድንቅ ነህ

እንዴት ታማኝ ነህ (፲፩x)