የሚገርመኝ መዳኔ ነው
አዝ፦ በመጀመሪያ ላመስግንህ ስለምን በሌላ ልጀምር በመሃከልም ልጨማምርበት ስለምን በሌላ ልቀጥል በመጨረሻ መደምደሚያዬ አምልኮ ይኸው ለአንተ ጌታዬ በመጨረሻ በመቋጫዬ ዝማሬ ይኸው ለአንተ ጌታዬ (፪x)
ያረክልኝ ነገር በዝቶ ስለምን ፊትህ ላጉረምርም አፌን በምሥጋና ልክፈት ማዘን በእኔ ላይ አያምርም ይኸው ምሥጋና ይኸው ዝማሬ አቀርባለሁ ዛሬ ይኸው ዕልልታ ይኸው ስግደቴ ለመድሃኒቴ
አዝ፦ በመጀመሪያ ላመስግንህ ስለምን በሌላ ልጀምር በመሃከልም ልጨማምርበት ስለምን በሌላ ልቀጥል በመጨረሻ መደምደሚያዬ አምልኮ ይኸው ለአንተ ጌታዬ በመጨረሻ በመቋጫዬ ዝማሬ ይኸው ለአንተ ጌታዬ (፪x)
ብዙ ነገር አርገህልኝ ጥቂቱን ብትከለክለኝ ያውም ለጥቅሜ ብለህ እንጂ መች ለጉዳት አሰብክብኝ በግማሽ ልቤ ምሥጋና አልሰጥም እኔ አልዘምርም ገብቶኛል የአንተ የአምላኬ አላማ ይኸው ምሥጋና
አዝ፦ በመጀመሪያ ላመስግንህ ስለምን በሌላ ልጀምር በመሃከልም ልጨማምርበት ስለምን በሌላ ልቀጥል በመጨረሻ መደምደሚያዬ አምልኮ ይኸው ለአንተ ጌታዬ በመጨረሻ በመቋጫዬ ዝማሬ ይኸው ለአንተ ጌታዬ (፪x)
አፌን ስከፍት በምሥጋና ሳቀርብ ለጌታ ሲሰጠው ማጉረምረም ማዘን መቆዘም አላገኙኝም ፈልገው ለቀውኝ ጠፉ ብቻዬን ቀረሁ ሰላም አገኘሁ ገና ያጡኛል ሳቀርብ ምሥጋና ላብዛ እንደገና
አዝ፦ በመጀመሪያ ላመስግንህ ስለምን በሌላ ልጀምር በመሃከልም ልጨማምርበት ስለምን በሌላ ልቀጥል በመጨረሻ መደምደሚያዬ አምልኮ ይኸው ለአንተ ጌታዬ በመጨረሻ በመቋጫዬ ዝማሬ ይኸው ለአንተ ጌታዬ (፪x)
በዚያ በክፉ ቀን በጨለማ (፪x) እግዚአብሔር ብቻ ጩኸቴን ሰማ (፪x) ደጃፌን ዘግቼ ያኔ የነገርኩህ (፪x) ያን ቀን ታስቦልኝ በእርሱ በዓይኔ አየሁህ (፪x)
አቤት ጌታዬ ምስኪኑን ሲረዳ አቤት ኢየሱሴ ሲደርስ ለተጐዳ አየሁ ጌታዬ ምስኪኑን ሲረዳ አየሁ ኢየሱሴ ሲደርስ ለተጐዳ
እርሱንማ በእውነት ለሚጠሩ የቅርብ እንጂ አይደለም የሩቅ ጌታንማ በእምነት ለሚጠሩ የቅርብ እንጂ አይደለም የሩቅ (፪x)
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x) እርካታዬ ስትከብር ሳይ (፪x) ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x) ተድላዬ ስትከብር ሳይ (፪x)
በጉባኤ መሃል ስትከብር እያየሁ እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ ሕዝብህ ሲያደንቅህ እያየሁ እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ አምሮብህ ተውበህ እያየሁ እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x) ሹመቴ ስትከብር ሳይ (፪x) ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x) ድምቀቴ ስትከብር ሳይ (፪x)
ችግረኛ ሲጮህ ሰምተህ ዝም አትልም (፪x) የምስኪኑን ውድቀት አይተህ እንዳላየህ አትሆንም (፪x) እጅህን ዘርግተህ ሁሉን ትረዳለህ (፪x) አደራረግህ ግሩም ነው ከሰው ልዩ ነህ (፪x)
አቤት ጌታዬ ምስኪኑን ሲረዳ አቤት ኢየሱሴ ሲደርስ ለተጐዳ አየሁ ጌታዬን ምስኪኑን ሲረዳ አየሁ ኢየሱሴ ሲደርስ ለተጐዳ
እርሱንማ በእውነት ለሚጠሩ የቅርብ እንጂ አይደለም የሩቅ ጌታንማ በእምነት ለሚጠሩ የቅርብ እንጂ አይደለም የሩቅ (፪x)
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x) እርካታዬ ስትከብር ሳይ (፪x) ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x) ተድላዬ ስትከብር ሳይ (፪x)
መቃብር ተከፍቶ እያየሁ እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ ድንጋይ ተንከባሎ እያየሁ እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ ዲያቢሎስ ሲረገጥ እያየሁ እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x) ሹመቴ ስትከብር ሳይ (፪x) ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x) ድንቀቴ ስትከብር ሳይ (፪x)
ምህረትህ ጌታዬ ምህረትህ ምህረትህ አምላኬ ምህረትህ ከአንተ የተነሳ ነው ለዚህ መድረሴ (፬x)
ምህረትህ እንዴት በዝቷል ከፍ ብሏል ለእኔስ ገኗል (፪x)
በበደሉ ምክንያት ጠፍቶ የነበረው ሰው ከጥፋት ጐዳና በፍቅርህ መለስከው የክህነቱን ስራ ኑሮው አድርጐታል ያዳነውን አምላኩን ሁሌ ይቀድሰዋል (፪x) ምህረትህ (፬x) ለእኔ በዝቷል ምህረትህ (፬x) ለእኔ በዝቷል
ብብዙዎችም መካከል (አመሰግንሃለሁ) ቸርነትህ ምድርን ሞልቷል (እዘምረዋለሁ) የስምህ ትርጉም ገብቶኛል (ሁሌ እጠራዋለሁ)
ብብዙዎችም መካከል (አመሰግንሃለሁ) ቸርነትህ ምድርን ሞልቷል (እዘምረዋለሁ) ኢየሱስ ማለት ገብቶኛል (ሁሌ እጠራዋለሁ)
ንጉሥ ንጉሥን ሲሽረው ኃያል ኃያሉን ሲያወርደው ጊዜው/አንዱ ሲያልፍ ሲተካ በሌላ ጌታ ኢየሱስ ግን ሁሌ የጌቶች ጌታ (፪x)
አይቼዋለሁ ኦሆሆ እኔም በኑሮዬ አሃሃ አመታት ኤለፉ አላለፈም ጌታዬ አይቼዋለሁ ኦሆሆ እኔም በኑሮዬ አሃሃ ዘመናት አለፉ አላለፈም ጌታዬ አይቼዋለሁ ኦሆሆ እኔም በኑሮዬ አሃሃ ኃያላን አለፉ አላለፈም ጌታዬ አይቼዋለሁ ኦሆሆ እኔም በኑሮዬ አሃሃ ብዙዎች አለፉ አላለፈም ጌታዬ
ሲመሽ ሲነጋ ጠዋት ማታ አመልከዋለሁ ይህን ጌታ (፪x) ሲመሽ ሲነጋ ጠዋት ማታ ሾመዋለሁ በከፍታ (፪x) ሲመሽ ሲነጋ ጠዋት ማታ አስበዋለሁ በመኝታ (፪x) ሲመሽ ሲነጋ ጠዋት ማታ እደነቃለሁ በዚህ ጌታ (፪x)
ስለሰራኸው ስራ ስላደረከው ነገር ስለሰራኸው መዳን ስላደረከው ተዓምር ምን እንከፍልሃለን ተመስገን (፬x)
እንዳንተ ያለ የለም (፪x) እንዳንተ ያለ የለም እላለሁ (፪x) እንዳንተ ያለ የለም (፪x) እንዳንተ ያለ የለም እላለሁ (፪x)
አዝ፦ ብርሃንህን በልቤ አብርተህልኛል ጨለማዬን ሁሉ ገፈህልኛል አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ ኢየሱስ ከልቤ ላመስግንህ ኢየሱስ ከልቤ ላመስግንህ (፪x)
በእኔ ላይ እንዳይሰለጥን የቀድሞው ጨለማ የዋይቶ የለቅሶ ድምጽ ከእንግዲህ እንዳይሰማ (፪x) ሕይወቴን ለውጧል ብርሃንህ በውስጤ ብሩህ ተስፋ አለኝ ለቀረው ዘመኔ አቅጣጫን ለውጧል አላማህ በውስጤ ብሩህ ተስፋ አለኝ ለቀረው ዘመኔ
አዝ፦ ብርሃንህን በልቤ አብርተህልኛል ጨለማዬን ሁሉ ገፈህልኛል አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ ኢየሱስ ከልቤ ላመስግንህ ኢየሱስ ከልቤ ላመስግንህ (፪x)
አዝ፦ አቤኔዘር አቤኔዘር እግዚአብሔር ረዳን አቤኔዘር አቤኔዘር እግዚአብሔር ረዳን እስካሁን እግዚአብሔር ረዳን እስካሁን እግዚአብሔር እረዳን (፪x) እኛም ደግሞ የረዳንን ልዑል እግዚአብሔርን እናመልካለን
. (1) . ኮረብቶች ወንዞችን አፈሰሱ በሸለቆችም መካከል ምንጮች ተከፈቱ ምድረበዳው ረሰረሰ ከጥማት ምድር ውኃ ፈለቃ እግዚአብሔር አምላክ የእኛን ጩኸት አደመጠ በእኛ ላይ ታወቀ
አዝ፦ አቤኔዘር አቤኔዘር እግዚአብሔር ረዳን አቤኔዘር አቤኔዘር እግዚአብሔር ረዳን ብቻውን እግዚአብሔር ረዳን ብቻውን እግዚአብሔር እረዳን (፪x) እኛም ደግሞ የረዳንን ልዑል እግዚአብሔርን እናመልካለን
ወጥመድ ቢዘረጋ አሃሃሃሃ ጉድጓድም ቢቆፍር ጠላቴ ሊይዘኝ ሊያጠፋኝ ቢሞክር ቢመስለኝም ምወድቅ ፈጽሞ ምጠፋ ጌታዬ ሆኖኛል የዘለዓለም ተስፋ አሜን
ስለዚህ አለሁ አልጠፋሁም ሸንበቆን አልተደገፍኩም ይረዳኛል ኃይሌ ነው በአምላኬ ቅጥሩን እዘላለሁ (፪x)
አምላክ ነህና አምላክ ነህና (፪x) ላምልክህ እንደገና (፬x) አምላክ ነህና ላምልክህ እንደገና አምላክ ነህና ላምልክህ እንደገና
አንዳንዶች የሰይጣን ቀንበሩ ከብዷቸው ጅባሬ ላይ ቀሩ ጠፍቶ ሚረዳቸው ሲያገለግሉ ሰይጣንን ደፋ ቀና ሲሉ ተሰብሮ ወጋቸው ምርኩዙ ጠፍተው በዚያው ቀሩ
እኔ ግን አለሁ አልጠፋሁም ቀንበር ከብዶኝ አልጐበጥኩም ቀና ብዬ እሄዳለሁ በአምላኬ ቅጥሩን እዘላለሁ
በፀጋሁ አለሁ አልጠፋሁም ቀንበር ከብዶኝ አልጐበጥኩም ቀና ብዬ እሄዳለሁ በአምላኬ ቅጥሩን እዘላለሁ
ከአንተ በቀር ሌላ ሌላ አምላክ ማነው ሌላ አምላክ ማነው (፪x)
ሳስብህ ደስ ይለኛል ኩራትም ይሰማኛል ከልቤ ደስታ ፈንቅሎ አዘለለኝ ወጣሁ ከእሮሮ (፭x)
አዝ፦ ታስገርማለህ እኔም ተገርሜያለሁ
ታስደንቃለህ በልቤ ተደንቄያለሁ
ታስደስታለህ እኔም ተደስቻለሁ
ታስፈነድቃለህ በልቤ ፈንድቄያለሁ
የእኔ ጌታ አምልኮ ሲያንስህ ነው
የእኔ ጌታ አክብሮት ሲያንስህ ነው (፪x)
ባከብርህ ይገባሃል ጌታ
ባከብርህ ይገባሃል ኢየሱስ
ባከብርህ ይገባሃል ጌታ
ባከብርህ ይገባሃል ኢየሱስ
አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ
ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ (፪x)
ፈረሱን ፈረሰኛውን በባሕር ጥለህልኛል
አቅም ያጣሁትን ክንድህ አሻግሮኛል
ከወጀቡ ወዲያ ቆሜ በድል እዘምራለሁ
ጉልበቴም ዝማሬዬም ሆነህልኝ ስላየሁ
አዝ፦ ታስገርማለህ እኔም ተገርሜያለሁ
ታስደንቃለህ በልቤ ተደንቄያለሁ
ታስደስታለህ እኔም ተደስቻለሁ
ታስፈነድቃለህ በልቤ ፈንድቄያለሁ
የእኔ ጌታ አምልኮ ሲያንስህ ነው
የእኔ ጌታ አክብሮት ሲያንስህ ነው (፪x)
ባከብርህ ይገባሃል ጌታ
ባከብርህ ይገባሃል ኢየሱስ
ባከብርህ ይገባሃል ጌታ
ባከብርህ ይገባሃል ኢየሱስ
አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ
ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ (፪x)
በእሳት በዳመና ተገልጠህ ጠላቴን ተመለከትከው
ወደ . (1) . ከባህና መዳኔን አፈጠንከው
እንደምትዋጋልኝ አይተው ሊሸሹ ሲማከሩ
ውሃው ጠላት ሆነባቸው ተከደነ ባሕሩ
አዝ፦ ታስገርማለህ እኔም ተገርሜያለሁ
ታስደንቃለህ በልቤ ተደንቄያለሁ
ታስደስታለህ እኔም ተደስቻለሁ
ታስፈነድቃለህ በልቤ ፈንድቄያለሁ
የእኔ ጌታ አምልኮ ሲያንስህ ነው
የእኔ ጌታ አክብሮት ሲያንስህ ነው (፪x)
ባከብርህ ይገባሃል ጌታ
ባከብርህ ይገባሃል ኢየሱስ
ባከብርህ ይገባሃል ጌታ
ባከብርህ ይገባሃል ኢየሱስ
አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ
ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ (፪x)
አዝ፦ አቤቱ ስራህ ግሩም ነው
ስራህ ግሩም ነው
አቤቱ ስራህ ግሩም ነው
ስራህ ግሩም ነው
ኢየሱስ ስራህ ግሩም ነው
ስራህ ግሩም ነው (፪x)
የወደቀን ማንሳት ስራህ ነው (፪x)
ማብቃት ለሽልማት ስራህ ነው (፪x)
የታሰረን መፍታት ስራህ ነው (፪x)
ፈቶም ነጻ ማውጣት ስራህ ነው (፪x)
እኔ ግን የሚገርመኝ
ሁልጊዜ የሚደንቀኝ
መዳኔ ነው መትረፌ ነው
ከሲዖል ማምለጤ ነው
እኔ ግን የሚገርመኝ
ሁልጊዜ የሚደንቀኝ
መዳኔ ነው መትረፌ ነው
ልጅህ መባሌ ነው
አዝ፦ አቤቱ ስራህ ግሩም ነው
ስራህ ግሩም ነው
አቤቱ ስራህ ግሩም ነው
ስራህ ግሩም ነው
ኢየሱስ ስራህ ግሩም ነው
ስራህ ግሩም ነው (፪x)
ባሕርን ማሻገር ስራህ ነው (፪x)
ፈርዖንን ማስጣል ስራህ ነው (፪x)
ማኖር በበረሃ ስራህ ነው (፪x)
እያፈለቅህ ውሃ ስራህ ነው (፪x)
እኔ ግን የሚገርመኝ
ሁልጊዜ የሚደንቀኝ
መዳኔ ነው መትረፌ ነው
ከሲዖል ማምለጤ ነው
እኔ ግን የሚገርመኝ
ሁልጊዜ የሚደንቀኝ
መዳኔ ነው መትረፌ ነው
ልጅህ መባሌ ነው
አዝ፦ አቤቱ ስራህ ግሩም ነው
ስራህ ግሩም ነው
አቤቱ ስራህ ግሩም ነው
ስራህ ግሩም ነው
ኢየሱስ ስራህ ግሩም ነው
ስራህ ግሩም ነው (፪x)
ከሰማይ መውረድህ ለእኔ ነው (፪x)
ደምህን ማፍሰስህ ለእኔ ነው (፪x)
መስቀል ላይ መሞትህ ለእኔ ነው (፪x)
ደግሞ መነሳትህ ለእኔ ነው (፪x)
ይህን ሳይ የሚገርመኝ
ሁልጊዜ የሚደንቀኝ
መዳኔ ነው መትረፌ ነው
ከሲዖል ማምለጤ ነው
ይህን ሳይ የሚገርመኝ
ሁልጊዜ የሚደንቀኝ
መዳኔ ነው መትረፌ ነው
ልጅህ መባሌ ነው
እኔ አለኝ ብዬ ለሰዎች ባወራ
ገልጬ ማሳየው ዘርዝሬ በተራ
እኔ አለኝ ብዬ ለሰዎች ባወራ
ገልጬ ማሳየው ቆጥሬ በተራ
ከአንተ በቀር ሌላ ነገር የለኝም
ሌላ ነገር የለኝም
ከአንተ በቀር ሌላ ነገር የለኝም
ሌላ ነገር የለኝም (፪x)
አዝ፦ ስለአንተ ብዘምር ልገልጽህ ብሞክር
ቃላት ብደረድር ባበዛ ብደምር
አይገልጽህም አንተን አሃሃሃ
አይገልጽህም አንተን (፪x)
ስለአንተ ብዘምር ልገልጽህ ብሞክር
ቃላት ብደረድር ባበዛ ብደምር
አይበቃህም ለአንተ አሃሃሃ
አይበቃህም ለአንተ (፪x)
አንደበት ያለው ቢዘምር ቢፈቀድለት ሊያወራ
መቼ ተተርኮ ያልቃል ብዙ ነው የአንተ ስራ
እስትንፋስ ያለው ቢደክም ግዑዙም ተራ ቢደርሰው
ጥበብህ ቁጥር የለውም ከተነገረው በላይ ነው
አዝ፦ ስለአንተ ብዘምር ልገልጽህ ብሞክር
ቃላት ብደረድር ባበዛ ብደምር
አይገልጽህም አንተን አሃሃሃ
አይገልጽህም አንተን (፪x)
ስለአንተ ብዘምር ልገልጽህ ብሞክር
ቃላት ብደረድር ባበዛ ብደምር
አይበቃህም ለአንተ አሃሃሃ
አይበቃህም ለአንተ (፪x)
መላዕክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቢሉም ሌሊትና ቀን
በሰማያዊ ቋንቋ ና ዜማ ብትመሰገን
ከሁሉ በፊት የነበርክ ዘመንህ አልተቆጠረም
ስለዚህ ዕድሜህን ያህን ተችሎት ማን ተናገረ
አዝ፦ ስለአንተ ብዘምር ልገልጽህ ብሞክር
ቃላት ብደረድር ባበዛ ብደምር
አይገልጽህም አንተን አሃሃሃ
አይገልጽህም አንተን (፪x)
ስለአንተ ብዘምር ልገልጽህ ብሞክር
ቃላት ብደረድር ባበዛ ብደምር
አይበቃህም ለአንተ አሃሃሃ
አይበቃህም ለአንተ (፪x)
የተማረውን ሕይወት አንተን የሚያሳየው
እንድትሰጠኝ ጌታ ሁልጊዜ ልመናዬ ነው
የተማረውን ምላስ አንተን የሚያከብረው
እንድትሰጠኝ ጌታ ሁልጊዜ ልመናዬ ነው
ልመናዬ ሌላ አይደለም ኦሆሆሆ
ልመናዬ ሌላ አይደለም ኦሆሆሆ
ልመናዬ ሌላ አይደለም ኦህህህ
ልመናዬ ሌላ አይደለም
በዚህ ጉብዝናዬ (፪x)
በዚህ ወጣትነት (፪x)
አንተው ታይበት (፪x)
ከዚህ ሌላ ምን እሻለሁ (፪x)
ከዚህ ወዲያ ምን እሻለሁ
ከዚህ ሌላ ምን እሻለሁ
በዚህ ጉብዝናዬ (፪x)
በዚህ ወጣትነት (፪x)
ፍቅርህ ማረከኝ (፪x)
ከዚህ ሌላ ምን እሻለሁ (፪x)
ከአንተ ወዲያ ምን እሻለሁ (፪x)
ስለፍቅር ቢወራ ባለሁበት
ምናገረው አለኝ የቀመስኩት
ለውድድር የማይቀርብ የማይመች
ነፍሴን ደግሞ ለራሱ የማረካት
እንዳንተ ያለ ፍቅር እኔ አላየሁም (፪x)
እንዳንተ ያለ ፍቅር እኔ አልሰማሁም (፪x)
ስለፍቅር ቢወራ ባለሁበት
ምናገረው አለኝ የቀመስኩት
ለውድድር የማይቀርብ የማይመች
ነፍሴን ደግሞ ለራሱ የማረካት
እንዳንተ ያለ ፍቅር እኔ አላየሁም (፪x)
እንዳንተ ያለ ፍቅር እኔ አልሰማሁም (፪x)
አዝ፦ አይደለህም ሰዎች እንደሚሉት
አይደለህም ብዙዎች እንደሚናገሩት
አይደለህም ሁኔታ እንደሚያወራው
አይደለህም ሰነፍ እንደሚናገረው
አምላኬ ቃልህ እንደሚልህ ነህ
እንደሚልህ ነህ ልክ እንደ ቃልህ
ጌታዬ ቃልህ እንደሚልህ ነህ
እንደሚልህ ነህ ልክ እንደ ቃልህ
እረሳሀን ተውከን ሲሉ ሰዎች እሰማለው
በምድር ላይ ሕይወት ብርቱ ፡ሰልፍ ሆኖባቸው
እኔ ግን አንተን ሳይ ተራራው ይከለልብኛል
ዘንድሮ ሰዎች ከሚሉህ ለእኔ ተለይተሃል (፪x)
አዝ፦ አይደለህም ሰዎች እንደሚሉት
አይደለህም ብዙዎች እንደሚናገሩት
አይደለህም ሁኔታ እንደሚያወራው
አይደለህም ሰነፍ እንደሚናገረው
አምላኬ ቃልህ እንደሚልህ ነህ
እንደሚልህ ነህ ልክ እንደ ቃልህ
ጌታዬ ቃልህ እንደሚልህ ነህ
እንደሚልህ ነህ ልክ እንደ ቃልህ
ደመና ባይታይ ዝናብም ባይዘንብ
የአየሩ ሁኔታ ህልውህን ባይገልጥህ
እኔ ግን አንተን ሳይ ሸለቆው ይሞላልኛል
ዘንድሮ ሰዎች ከሚያዩህ ለእኔ ተለይተሃል (፪x)
አዝ፦ አይደለህም ሰዎች እንደሚሉት
አይደለህም ብዙዎች እንደሚናገሩት
አይደለህም ሁኔታ እንደሚያወራው
አይደለህም ሰነፍ እንደሚናገረው
አምላኬ ቃልህ እንደሚልህ ነህ
እንደሚልህ ነህ ልክ እንደ ቃልህ
ጌታዬ ቃልህ እንደሚልህ ነህ
እንደሚልህ ነህ ልክ እንደ ቃልህ
አምላኬ ቃልህ እንደሚልህ ነህ
እንደሚልህ ነህ ልክ እንደ ቃልህ
ጌታዬ ቃልህ እንደሚልህ ነህ
እንደሚልህ ነህ ልክ እንደ ቃልህ (፪x)
አዝ፦ ከአንተ በቀር ብዙ ብዙ ብዙ
ብዙ ጌቶች ገዝተውን ነበር
እኛስ አላየንም እንደአንተ የሚሆን
እጅግ ወደንሃል ለዘለዓለም ግዛን (፪x)
ክብር ይሁን ከክብርም በላይ
ሞገስ ከሞገሥም በላይ
ጌታ ነህና ኤልሻዳይ (፪x)
ሃሳብህ የሰላም ነው ሁልጊዜ ለሕዝብህ
አላማህ ፍቅር ነው ጌታ ለልጆችህ
የልብህ እርካታ ሰዎችን ማዳን ነው
በቤትህ መኖር ጌታ ሕይወትን ማትረፍ ነው (፪x)
አዝ፦ ከአንተ በቀር ብዙ ብዙ ብዙ
ብዙ ጌቶች ገዝተውን ነበር
እኛስ አላየንም እንደአንተ የሚሆን
እጅግ ወደንሃል ለዘለዓለም ግዛን (፪x)
ክብር ይሁን ከክብርም በላይ
ሞገስ ከሞገሥም በላይ
ጌታ ነህና ኤልሻዳይ (፪x)
ለጥያቄዎች ሁሉ በቤትህ መልስ አለ
ለሁሉም እንደአመሉ ትናገረዋለህ
ወደ አንተ የመጣ ማነው ሳያርፍ የሄደ
ቤትህን ወደድነው ጌታ/ኢየሱስ ለሁሉም ዕረፍት አለ (፪x)
አዝ፦ ከአንተ በቀር ብዙ ብዙ ብዙ
ብዙ ጌቶች ገዝተውን ነበር
እኛስ አላየንም እንደአንተ የሚሆን
እጅግ ወደንሃል ለዘለዓለም ግዛን (፪x)
ክብር ይሁን ከክብርም በላይ
ሞገስ ከሞገሥም በላይ
ጌታ ነህና ኤልሻዳይ (፪x)
ለእርስትህ የምትራራ ሕዝብህን ምታከብር
ለጠላት መላገጫ አሳልፈህ አትሰጥም
እንዳንተ የሚሆን መልካም ትሁት እረኛ
በሕይወት ዘመናችን ኢየሱስ አላየንም እኛ (፪x)
አዝ፦ ከአንተ በቀር ብዙ ብዙ ብዙ
ብዙ ጌቶች ገዝተውን ነበር
እኛስ አላየንም እንደአንተ የሚሆን
እጅግ ወደንሃል ለዘለዓለም ግዛን (፪x)
ክብር ይሁን ከክብርም በላይ
ሞገስ ከሞገሥም በላይ
ጌታ ነህና ኤልሻዳይ (፪x)